Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የተቀደሰ ሕይወት

    የተቀደሱ መርሆዎችን ወደ ሕይወታችን በማምጣት የእግዚአብሔርን ቅዱስ ቃል እናጥና፡፡ በየእለቱ ሥህተቶቻችንን በማረም በየዋህነትና ራስን ዝቅ በማድረግ በእግዚአብሔር ፊት እንመላለስ፡፡ በራስ ወዳድነት ትዕቢት ነፍስን ከእግዚአብሔር አንለይ፡፡ ራስህን ከሌሎች የተሻልክ አድርገህ በማሰብ የበላይነትን ስሜት አታንፀባርቅ፡፡ «የቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ፡፡” ሰላምና እረፍት የሚመጣልህ ፈቃድህን ለክርስቶስ ፈቃድ ስታስገዛ ነው፡፡ ያኔ የክርስቶስ ፍቅር ምስጢራዊ የሆኑ የድርጊት ምንጮችን ለአዳኙ ምርኮ አድርጎ በማምጣት በልብ ውስጥ ይገዛል፡፡ ችኩልና በቀላሉ ቱግ የሚል ስሜት በክርስቶስ የፀጋ ዘይት ለስልሶ የሚገዛ ይሆናል፡፡ ይቅር የተባሉ ኃጢአቶች ስሜት አእምሮን የሚያልፍ ሰላም ያመጣል፡፡ ክርስቲያናዊ ፍጽምናን የሚቃወም ነገርን ሁሉ ለማሸነፍ ልባዊ ጥረት ይደረጋል፡፡ ልዩነት ይጠፋል፡፡ አንድ ጊዜ በዙሪያው ባሉ ሰዎች ላይ ስህተትን ያይ የነበረው ሰው አሁን በእራሱ ባሕርይ ውስጥ እጅግ ብዙ ስህተቶች እንዳሉት ያያል፡፡MYPAmh 54.2

    እውነትን የሚሰሙና ከዚህ በፊት የክርስቶስ ተቃዋሚ ሆነው ይኖሩ እንደ ነበር የሚያምኑ ሰዎች አሉ፡፡ በኃጢአት ኩነኔ ሥር መኖራቸውን በመገንዘብ ለኃጢአታቸው ንስሀ ይገባሉ፡፡ በኢየሱስ የማዳን ሥራ በመደገፍና በእርሱ እውነተኛ እምነት በማመን ለኃጢአታቸው ይቅርታ ያገኛሉ፡፡ ክፉ ማድረግን ሲተውና መልካም ማድረግን ሲማሩ በፀጋና እግዚአብሔርን በማወቅ ያድጋሉ፡፡ ከዓለም ለመለየት ራስን መስዋዕት ማድረግ እንዳለባቸው ያያሉ፡፡ የሚያስከፍላቸውን ዋጋ በሙሉ ከቆጠሩ በኋላ ክርስቶስን ማግኘት ከቻሉ ሌላውን ሁሉ እንደ ዋጋ ቢስ ይቆጥሩታል፡፡ ራሳቸውን ከክርስቶስ ሠራዊት ጋር አሰልፈዋል፡፤ ከፊታቸው ወዳለው ጦርነት በደስታና በድፍረት በመግባት ከተፈጥሮ ዝንባሌዎቻቸውና ራስ ወዳድ ፍላጎቶቻቸው ጋር ጦርነት በመግጠም ፈቃዳቸውን ለክርስቶስ ፈቃድ ያስገዛሉ፡፡ በየቀኑ ሊታዘዙት የሚያስችለውን ፀጋውን ይሻሉ፡፡ ያኔ እርዳታና ብርታት ያገኛሉ፡፡ ይህ እውነተኛ መለወጥ ነው፡፡ አዲስ ልብ የተሰጠው ግለሰብ ትሁትና አመስጋኝ በሆነ መታመን በኢየሱስ እርዳታ ላይ ይደገፋል፡፡ በሕይወቱ የጽድቅን ፍሬ ይገልጣል፡፡ ከዚህ በፊት ራሱን ይወድ ነበር፡፡ ዓለማዊ ደስታ ደስታው ነበር፡፡ አሁን ግን ጣኦቱ ከዙፋኑ ወርዶ እግዚአብሔር የበላይ ገዥ ሆኗል፡፡ ከዚህ በፊት ይወዳቸው የነበራቸውን ኃጢአቶች ዛሬ ይጠላቸዋል፡፡ በጽናትና በማይነቃነቅ ውሳኔ የቅድስናን መንገድ ይከተላል፡፡ The Youth’s Instructor, Sept, 26,1901.MYPAmh 54.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents