Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ለእግዚአብሔር ሕዝቦች ወጥመድ

    የወቅቱን እውነት እናምናለን በሚሉት መካከል የፋሽንና የታይታ ፍቅር ስናይ የእግዚአብሔር ህዝቦች ካለፈው ታሪክ ምንም አይማሩምን? ብለን በሀዘኔታ እንጠይቃለን። የራሳቸውን ልብ የሚያውቁ በጣም ጥቂት ናቸው። ከንቱና ፌዘኛ የሆኑ ፋሽን ወዳጆች የክርስቶስ ተከታዮች ነን ይላሉ። ነገር ግን አለባበሳቸውና ንግግራቸው አእምሮአቸውን የሞላውና ፍቅር ያስያዛቸው ምን እንደሆነ ይገልጻል።MYPAmh 230.3

    ሕይወታቸው ከዓለም ጋር ወዳጆች መሆናቸውን ይገልፃል! ዓለምም እነርሱ የራሱ እንደሆኑ ይናገራል። የእግዚአብሔርን ፍቅር የቀመሰ ሰው እንዴት በፋሽን ከንቱነት ሊረካ ይችላል? የዚያ የዋህና ትሁት የሆነው አዳኝ ተከታዮች እንደሆኑ የሚናገሩ ሰዎች ከዓለም አለባበስ ጋር ለመመሳሰል ከልባቸው ሲሹ ሳይ ልቤ ያዝናል። እግዚአብሔርን እናመልካለን ይበሉም እንጂ ከማያምኑት በምንም አይለዩም። መንፈሳዊ ሕይወት አያስደስታቸውም። ለታይታ የመልበስ ዓላማን ከግብ ለማድረስ ጊዜአቸውና ገንዘባቸው ተሰውቷል።MYPAmh 230.4

    በአለባበስ የሚገለጥ ኩራትና ከመጠን ያለፈ ብክነት በተለይ ሴቶችን እያጠቃ ያለ ኃጢአት ነው። በመሆኑም የሐዋሪያው “እንዲሁም ደግሞ ሴቶች በሚገባ ልብስ ከእፍረትና ራሳቸውን ከመግዛት ጋር ሰውነታቸውን ይሸልሙ። እግዚአብሔርን እንፈራለን ለሚሉት ሴቶች እንደሚገባ መልካም በማድረግ እንጂ በሽሩባና በወርቅ ወይም በእንቁ ወይም ዋጋው እጅግ በከበረ ልብስ አይሸለሙ።” ያለው መመሪያ እነዚህን ሴቶች በቀጥታ ይመለከታቸዋል።MYPAmh 230.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents