Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    እንቅፋቶችን መጋፈጥ

    በመንገዳችን ላይ ያሉትን እንቅፋቶች በሙሉ በመጋፈጥ እያንዳንዱን ተራ በተራ ልናሸንፍ ይገባል፡፡ የመጀመሪያውን ፈተና ካሸነፍን ሁለተኛውን ለመጋፈጥ ጥንካሬ እናገኝና እያንዳንዱ ቀጣይ ጥረቶች ወደፊት ለመቀጠል የተሻሉ ይሆናሉ፡፡ ወደ ኢየሱስ በመመልከት አሸናፊዎች እንሆናለን፡፡ ዓይኖቻችንን በችግሮቻችን ላይ ስናደርግና ለትክክለኛ ነገር ልባዊ ጦርነት ከማድረግ ወደ ኋላ ስንል ደካሞችና እምነት የለሾች እንሆናለን፡፡MYPAmh 36.4

    እርምጃ ደረጃ በደረጃ ሲኬድ ከፍታው ወደ ላይ ይወጣና በመጨረሻ የተራራው ጫፍ ላይ ይደረሳል፡፡ በሕይወትህ ዘመን ልትፈጽመው ባለህ የሥራ ብዛት ልብህ አይሸበር፡፡ ሁሉንም በአንድ ጊዜ እንድትፈጽመው አትጠየቅም፡፡ እያንዳንዱ የህሊና ኃይልህ ወደ እያንዳንዱ ቀን ሥራህ መሄድ አለበት:: እያንዳንዱን መልካም አጋጣሚ ማሻሻል፣ እግዚአብሔር የሚሰጥህን እርዳታ ማድነቅና በእድገት መሰላል ላይ ደረጃ በደረጃ መውጣት አለብህ፡፡ እግዚአብሔር አንድ ቀን እንደ ሰጠህ በማስታወስ እያንዳንዱን ቀን ተራ በተራ ኑርበት፡፡ የሰማይ መዝገቦች የተሰጡህን እድሎችና መልካም አጋጣሚዎች ምን ያህል ዋጋ እንደሰጠሃቸው ያሳያሉ፡፡ ስለዚህ ከእግዚአብሔር የተሰጠህን እያንዳንዱን ቀን ስታሻሽል በመጨረሻ ጌታ «አንተ መልካምና ታማኝ ባሪያ፣ በጥቂት ታምነሃልና በብዙ እሾምሃለሁ» ይልሃል፡፡—The Youth’s Instructor, January 5, 1893.MYPAmh 36.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents