Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ሰይጣን በእግዚአብሔር

    ህዝቦች ላይ በሚያደርገው የመጨረሻው ዘመቻ እርሱ መሆኑን እንዳያውቁ በማድረግ ማታለያዎቹን እያዘጋጀ ነው፡፡ በ2ኛ ቆሮ 11፡14 ላይ «በዚህ አትደነቁ፣ ሰይጣን እራሱ በብርሃን መልአክ ተመስሎ ይመጣል“» ተብሏል፡፡ አንዳንድ የተታለሉ ነፍሳት ሰይጣን የለም ቢሉም እነርሱን የክርስቶስ ምሳሌነት እንደሚያሳየን ድልን የማግኘት ብቸኛው ተስፋችን የሰይጣንን ጥቃት ያለማቋረጥ መከላከል ነው፡፡ MYPAmh 40.2

    በፈተና ውስጥ በነፍሳት ጠላት ላይ ድልን የተቀዳጀው ኢየሱስ ሰይጣን በሰብዓዊ ዘር ላይ ያለውን ኃይል ያስተውላል፤ በኛ ፋንታም አሸንፎታል፡፡ እንደ አሸናፊ ለኛም የእርሱን የማሸነፍ እድል ሰጥቶናል፡፡ የሰይጣንን ፈተና በመቋቋም ጥረታችን የኛን ድክመት ከርሱ ብርታት ጋር፣ የኛን ዋጋ ቢስነት ከርሱ ሥራ ጋር የማገናኘት እድል ሰጥቶናል፡፡ በፈተናው ጥንካሬ ሥር በርሱ ብርታት በመቆም በርሱ ሃያል ስም እርሱ እንዳሸነፈ እኛም እናሸንፋለን፡፡ ምርኮኛው በማድረግ በእነርሱ አማካይነት ከፍተኛ ሥራ እየሰራ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ህዝቦች ብርታታቸው በክርስቶስ ሲሆን በእርሱ ሊኖራቸው የሚችለውን ኃይል ከእነርሱ የበለጠ ያውቃል፡፡ ራሳቸውን ዝቅ በማድረግ ብርቱ አሸናፊ የሆነውን እርዳታ ሲሹ በእውነት ላይ ደካማዎቹ ክርስቲያኖች እንኳን በክርስቶስ ላይ በፅናት በመደገፍ በተሳካ ሁኔታ ሰይጣንንና ሰራዊቶቹን በሙሉ መመከት ይችላሉ፡፡ MYPAmh 40.3

    ሰይጣን ፈተናዎቹን ይዞ በግልጽ በድፍረት እንዳይመጣ ብልጥ ነው፡፡ ምክንያቱም በግልጽ ከመጣ የክርስቲያናት የደከሙ ኃይሎች ይነሳሱና ብርቱ ነፃ አውጪ በሆነው በክርስቶስ እንዳይደገፉ ስለሚፈልግ ነው፡፡ ነገር ግን ሰይጣን ሳይታይ በመምጣት ሥራውን በስውር የአምልኮ መልክ ባላቸው በአመፃ ልጆች አማካይነት ይሰራል፡፡ ሰይጣን ኃይሉን በመጠቀም የእግዚአብሔርን ልጆች እስከ ማስፈራራት፣ መፈተንና ማታለል ይሄዳል፡፡ ኢየሱስን ፊት ለፊት ለመጋፈጥ፣ ለመፈተንና ለማወክ ድፍረት የነበረውና በክንዶቹ ተሸክሞት እስከ ቤተ መቅደሱ ጫፍ ሊያወጣው የቻለው እንዲሁም እጅግ ባነሱትና ለሰይጣን ተንኮልና ብርታት እውቀት በሌላቸው በዚህ ትውልድ ላይ ኃይሉን በአስደናቂ ሁኔታ ይጠቀማል፡፡MYPAmh 40.4

    የእርሱን ፈቃድ ለመፈፀም በተፈጥሮ የሚያዘነብሉ ሰዎች አካል ላይ ተጽእኖ ያሳድራል፡፡ ሰይጣን እንደ ልብ ወለድ ነገር ተደርጎ በሚወሰድበት ጊዜ በጣም ራሱን ከፍ ከፍ ያደርጋል፡፡ ሰዎች አቅልለው ሲያዩትና የህፃን አስተሳሰብ ያለው መግለጫ ሲሰጠው ወይም እንደ የሆነ እንስሳ ተደርጎ ሲገለጽ በጣም ይመቸዋል፡፡ ስለ እርሱ እንዲህ ዝቅ አድርጎ ሲታሰብ አእምሮዎች እርሱ በጥበብ ላቀደው እቅድ ያልተዘጋጁ ይሆኑና ሁል ጊዜ ይሳካለታል:: የእርሱ ኃይልና ተንኮሉ ከተስተዋለ አእምሮዎች ሊቋቋሙት በደንብ ይዘጋጃሉ፡፡MYPAmh 40.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents