Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የተስተካካለ ግንዛቤ መሻት

    ከማንኛውም ጉዳይ የበለጠ ትኩረት ተሰጥቶበት በረጋ መንፈስና ስሜታዊ ባልሆነ ግንዛቤ ሊታይ የሚገባው ነገር ቢኖር ጋብቻ ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ ምክር የሚያሻው ጊዜ ቢኖር ሁለት ሰዎችን ለህይወት የሚያጣምር እርምጃ ከመወሰዱ በፊት ነው። ብዙዎችን የፍቅር በሽተኛነት ስሜት ይይዛቸውና ወደ ጥፋት ይመራሉ። ከማንኛውም ነገር ይልቅ ወጣቶች እውቀት የሚጎድላቸው በዚህ ጉዳይ ላይ ነው። ማመዛዘን የሚያቅታቸውም በዚህ ጉዳይ ላይ ነው። የጋብቻ ጉዳይ የምዋረት ኃይል ይመስላቸዋል። ራሳቸውን ለእግዚአብሔር አይሰጡም። ስሜታቸው ተጠልፏል። ከዚህም የተነሣ በእነርሱ ጉዳይ ሌላ ሰው ጣልቃ የሚገባባቸው ስለሚመስላቸው በስውር ወደ ፊት መቀጠል ይጀምራሉ።MYPAmh 283.1

    የብዙዎች ግንኙነትና ጋብቻ የሚፈፀምበት መንገድ እግዚአብሔር ብቻ የክፋቱን መጠን ለሚያውቃቸው ስቃዮች ምክንያት ነው። በዚህ ዓለት ላይ የብዙዎች ነፍሳት መርከብ ተጋጭታለች። በፅኑነታቸው የተመሰከረላቸው ታዋቂ ክርስቲያኖች፣ ሌሎች ጉዳዮችን የማመዛዘን ችሎታ ያላቸው ሁሉ በዚህ ነጥብ ላይ አስፈሪ ስህተት ይፈጽማሉ። በምክንያት ሊለወጥ የማይችል የተወጠነ ግትር አቋም ያሳያሉ። በሰብዓዊ ግፊትና ስሜቶች ያለ መጠን ከመማረካቸው የተነሣ ከእግዚአብሔር ጋር የቅርብ ግንኙነት የመፍጠርና መጽሐፍ ቅዱስን የመመርመር ፍላጎት የላቸውም።MYPAmh 283.2

    ሰይጣን በምን አይነት ጉዳዮች ማተኮር እንዳለበት ያውቃል። በመሆኑም ነፍሳትን በማጥመድ ወደ ጥፋት ሊመራቸው በሚጠቀምባቸው መሣሪያዎች ሁሉ የተንኮል ጥበቡን ይገልጣል። እያንዳንዱን እርምጃ እየተከተለ ሐሳብ ያቀርባል። ብዙ ጊዜ የእግዚአብሔርን ቃል ምክር ከመፈለግ ይልቅ እነዚህ ሐሳቦች ተቀባይነት ያገኛሉ። ይህ በጥንቃቄ የተጠላለፈ አደገኛ መረብ ወጣቶችንና ያልተጠነቀቁትን ለማጥመድ በብልጠት ተዘጋጅቷል:: ብዙ ጊዜ በብርሃን ሽፋን ሊደበቅ ይችላል። ነገር ግን የእርሱ ምርኮኞች የሚሆኑ ወደ ብዙ ሃዘን ይገባሉ። በመሆኑም በየቦታው የሰዎችን ጉስቁልና እናያለን።MYPAmh 283.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents