Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ለወጣቶች የተሰጡ ተስፋዎች

    ክርስቶስን የሚከተሉ ወጣቶች ከፊታቸው ጦርነት ይጠብቃቸዋል። ከዓለም ለመውጣትና የክርስቶስን ሕይወት ለመቅዳት በሚያደርጉት ጥረት የሚሸከሙት የየእለት መስቀል አለ። ኢየሱስን ማልደው ለሚሹ የተገቡ ውድ ቃል ኪዳኖችን የሚገልፁ ነገሮች ተመዝግበው አሉ። ጥበብ የሰውን ልጆች እንዲህ ብላ ትጣራለች፦ “የሚወዱኝን እወዳቸዋለሁ! ማልደው የሚሹኝም ያገኙኛል።” ምሳሌ 8፡17::MYPAmh 243.3

    “ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኖራችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ፀጋ ፈፅማችሁ ተስፋ አድርጉ። እንደሚታዘዙ ልጆች ባለማወቃችሁ አስቀድሞ የኖራችሁበትን ምኞት አትከተሉ። ዳሩ ግን የጠራችሁ ቅዱስ እንደሆነ ሁሉ እናንተም በንግግራችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ።” 1ኛ ጴጥ 1፡13-15። “ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ፀጋ ተገልጧልና! ይህም ፀጋ ኃጢአታኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድሃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል። መድሃኒታችንም ከዓመፃ ሁሉ እንዲቤዠን መልካሙን ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ህዝብ ለራሱ እንዲያነፃ፣ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።” ቲቶ 2፡11 -14። Counsels to Teachers, Parents & Students, P. 325-330.MYPAmh 243.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents