Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    መሪ መርሆዎች

    ልብ የኢየሱስ ነው። ለነፍስ ዘላለማዊ ዋጋ ከፍሏል፣ ለእኛ በአባቱ ፊት እንደተለማማጭ ለማኝ ሳይሆን የራሱ የሆነውን እንደሚጠይቅ አሸናፊ ያማልድልናል። ለእኛ ሊያማልድልን ሁልጊዜ ስለሚኖር ፈፅሞ ሊያድን ይችላል። ወጣት ልብ ለእግዚአብሔር ሊሰጥ ከሚችል ሥጦታ ሁሉ እጅግ ዋጋ ያለው ውድ ስጦታ ነው። እናንተነታችሁንና፣ ያላችሁን ችሎታ ሁሉ ለእርሱ በፈቃዳችሁ ቅዱስ ስጦታ አድርጋችሁ እንድትሰጡ ከእግዚአብሔር የተሰጣችሁ ቅዱስ ስጦታ ነው። እርሱ አስቀድሞ ያልሰጣችሁን ነገር ለእርሱ መልሳችሁ መስጠት አትችሉም። ስለዚህ ልብ ለእግዚአብሔር በሚሰጥበት ጊዜ እርሱ ራሱ የገዛውንና የእርሱ የሆነውን መልሶ ለራሱ ስጦታ መስጠት ነው።MYPAmh 260.1

    የወጣቶችን ጊዜ፣ ፍቅራቸውንና ብርታታቸውን ይገባናል የሚሉ ብዙዎች ናቸው። ሰይጣን ወጣቶችን ንብረቴ ናቸው ይላል፣ ብዘዎችም ያላቸውን ችሎታና መክሊት ለእርሱ ይሰጣሉ። ዓለምም የወጣቶችን ልብ ይፈልጋል። ነገር ግን ያ ልብ የግለሰቡ ሳይሆን የአዳኙ ንብረት ነው። ለዓለም ከተሰጠ በጭንቀት፣ በሀዘንና ተስፋ መቁረጥ ይሞላል! ንፅህና የሌለውና የተበከለ ይሆናል። ለእግዚአብሔር የሆኑትን የልባችሁን ፍቅርና አገልግሎት ለዓለም መስጠት እጅግ አስከፊ የሆነ መቀማት ነው። ልባችሁን ለደስታ ፍለጋ ሰጥታችሁ ትርፍ ማግኘት አትችሉም።MYPAmh 260.2

    የጽድቅ ጠላት በሁሉም የሕይወት ሁኔታዎች እያንዳንዱን የደስታ ዓይነት ለወጣቶች አዘጋጅቷል። እነዚህ የመደሰቻ አይነቶች የሚገኙት በሕዝብ በተጨናነቁ ከተማዎች ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅ በሚኖርበት በእያንዳንዱ ቦታ ላይ ነው። ሰይጣን ወጣቶችን እንደ ወታደሮች በራሱ ወገን ማሰለፍ ይፈልጋል። የክፉ መናፍስት አለቃ ከምን ጋር መስራት (ጊዜ ማጥፋት) እንዳለበት ያውቃል። ወጣቶቻችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ካላቸው ፍቅር ሊለዩ የሚችሉበትን ወጎችና መደሰቻዎች በማዘጋጀት ጥበቡን አሳይቷል…።MYPAmh 260.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents