Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ብርሃን ተሸካሚዎች ሁኑ

    ወደ ምትሄድበት ሁሉ ብርሃንን ተሸከም:: የዓላማ ጽናት እንዳለህ አሳይ:: ውሳኔ የሌለህና በክፉ ጓደኞች ተፅእኖ ወዲያና ወዲህ የምትዋዥቅ እንዳልሆንክ አሳይ:: MYPAmh 23.1

    እግዚአብሔርን ከማያከብሩ ሰዎች አስተያየት ጋር በቀላሉ አትስማማ፤ ነገር ግን በ•ነርሱ ተሃድሶን ለማምጣት፣ ከስህተታቸው ለመመለስና ነፍሳትን ከክፉ ለማዳን ፈልግ:: ወደ ፀሎት ተመለስ፣ በትህትናና ዝቅ ባለ መንፈስ ራሳቸውን የሚቃወሙትን ለማሳመን ሞክር፤ ከስህተት የተመለሰና ከክርስቶስ አርማ ሥር የመጣ አንድ ነፍስ በሰማይ ታላቅ ደስታን ከማምጣቱም በላይ ባንተ የፍስሐ ዘውድህ ላይ ኮከብ ያኖርልሃል:: የዳነ ነፍስ ከአምላክ ጋር ካለው ግንኙነት የተነሳ ሌሎች ነፍሳትን ወደ ደህንነት እውቀት ያመጣል:: በዚህ ሁኔታ ሥራው እየተባዛ ይሄዳል:: የተሰራውን ሥራ መጠን በትክክል የሚገልፁት በፍርድ ቀን የሚገለፁ ነገሮች ናቸው::MYPAmh 23.2

    መስራት የምትችለው ጥቂት እንደሆነ በማሰብ ለጌታ ላለመስራት አታመንታ:: ከአንተ ጥረት ጋር እግዚአብሔር ስለሚሰራ ማድረግ የምትችለውን ጥቂት ነገር በታማኝነት አድርግ:: ወደ ጌታ ደስታ ለመግባት እንደተገባው ሰው አድርጎ ስምህን በህይወት መፅሐፍ ይጽፈዋል:: መከሩ ዝግጁ ስለሆነ 1 2 እግዚአብሔር ሠራተኞችን እንዲያስነሳ ተግተን እንፀልይ:: መከሩ ብዙ ነው፣ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው::MYPAmh 23.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents