Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    መንፈስን መግዛት

    በዝምታ ውስጥ አስደናቂ ኃይል አለ። ሰዎች ትዕግሥት የጎደላቸውን ቃላት ሲውረወሩባችሁ አፀፋውን አትመልሱ:: ለተቆጣ ሰው የሚወረወሩ የአፀፋ ቃላት የፈረስን ፍጥነት ለመጨመር እንደሚያገለግል ጅራፍ በመሆን በተለምዶ ቁጣውን ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንዲደርስ ያደርጉታል። ነገር ግን የዝምታ ምላሽ የተሰጠው ቁጣ በቶሎ ይሞታል። ክርስቲያን ሻካራና ትዕግስት የሌላቸውን ቃላት እንዳይናገር ለምላሱ ልጓም ያድርግ። ለምላሱ ልጓም ካደረገለት እንዲያልፍ በተጠራበት በእያንዳንዱ የትዕግስት ፈተና አሸናፊ ይሆናል።MYPAmh 91.1

    ኃይል ሁሉ በሰማይና በምድር ያለውን አጥብቀህ ያዘው። ብዙ ጊዜ ትዕግሥትና መረጋጋትን ማሳየት ቢያቅትህም መታገልህን አታቋርጥ። ከመጀመሪያው ይበልጥ በአሁኑ ሰዓት በማንኛውም ቁጣ ቀስቃሽ ሁኔታ ውስጥ ታጋሽ ለመሆን ወስን። ዓይኖችህን ከመለኮታዊ ምሳሌህ በፍፁም አታንሣ።MYPAmh 91.2

    ሰው በራሱ ብርታት መንፈሱን መግዛት አይችልም። ነገር ግን በክርስቶስ አማካይነት ራሱን የመግዛት ኃይል ሊያገኝ ይችላል። በክርስቶስ ብርታት አስተሳሰብንና ቃላቶቹን ለእግዚአብሔር ፈቃድ ማስገዛት ይችላል። የክርስቶስ ኃይማኖት ስሜቶችን በማመዛዘን፣ ቁጥጥር ሥር በማድረግ ምላስን ይገራል። በእርሱ ተፅዕኖ ሥር ፈጣን ቁጣ ይቀዘቅዝና ልብ በትዕግሥትና በጨዋነት ይሞላል። Review and Herald, October 31, 1907.MYPAmh 91.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents