Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ውስጣዊ ሽልማት

    የክርስቶስ ተከታዮች እግዚአብሔር ታላቅ ዋጋ እንዳለው የሚገልፀውን የዋህና ፀጥ ያለ መንፈስ ያለበትን ውስጣዊ ሽልማትን ለማግኘት ይሹ ይሁን ወይስ የምህረት በር ከመዘጋቱ በፊት ያሉትን ጥቂት አጭር ሰዓታት ለታይታ በማለት አለ አስፈላጊ ጥረት እያደረጉ ያባክኑት ይሆን? ጌታ ለዓለም በረከትና ለፈጣሪ ክብር የሚያመጣ ደስተኛ ህይወት መኖር የሚያስችላትን የአእምሮና የሞራል ብርታትን ለማግኘት ሁልጊዜ አእምሮዋንና ልብዋን ለማሻሻል የምትሻን ሴት ይፈልጋል።MYPAmh 231.2

    የወቅቱን እውነት እናምናለን የሚሉትን የዛሬ ወጣቶች ለእውነት ብለው ራሳቸውን ለመካድ ፈቃደኛ መሆናቸውን ወይም አለመሆናቸውን እጠይቃቸዋለሁ። አንድን ልብስ ወይም ጌጣጌጥ ወይም ምቾት በሚሹበት ጊዜ ለዚያ ነገር የሚያወጡትን ወጪ የእግዚአብሔር መንፈስ ትክክል መሆን አለመሆኑን ማረጋገጫ እንዲሰጥ ጉዳዩን በፀሎት በጌታ ፊት ያስቀምጡታልን? ልብሶቻቸውን በሚያዘጋጁበት ጊዜ የሚያምኑትን እምነት እንዳያዋርዱ ይጠነቀቃሉን? በዚህ ጉዳይ ላይ በዋለው ጊዜ የእግዚአብሔር በረከት እንዲወርድ ይሻሉን? የቤተክርስቲያን አባል መሆን አንድ ነገር ሲሆን ከክርስቶስ ጋር አንድ መሆን ግን ሌላ ነገር ነው። ያልተቀደሱና ዓለምን የሚወዱ የኃይማኖት ሰዎች ለክርስቶስ ቤተክርስቲያን እጅግ አስከፊ የሆነ ድክመት ከሚያስከትሉ ነገሮች አንዱ ናቸው።MYPAmh 231.3

    በዓለማችን በአሁኑ ዘመን ከዚህ በፊት ሆኖ የማያውቅ የደስታ እሽቅድምድም አለ። በየቦታው የሞራል ውድቀትና በግድየለሽነት የገንዘብ ብክነት ይታያል። ህዝብ ራሱን ለማዝናናት ጉጉት አለው:: አእምሮ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ለማሰላሰልና የተገራ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማድረግ ካልተለማመደ የማይጠቅምና ሞኝ ይሆናል። የድንቁርና ስሜት ይታያል። እግዚአብሔር እያንዳንዱ ነፍስ እንዲያድግ፣ እንዲሞረድ፣ ከፍ ያለና የከበረ እንዲሆን ይሻል። ነገር ግን ብዙ ጊዜ በፋሽን አሸብርቆ ለመታየትና ጥልቀት ለሌለው ደስታ ሲባል ዋጋ ያለው ስኬት ችላ ይባላል። ሴቶች ነፍሶቻቸው በፋሽን እንዲራቡና እንዲቀጭጩ ይፈቅዱና ለህብረተሰቡ በረከት በመሆን ፋንታ እርግማን ይሆናሉ። Review and Herald December 6,1881.MYPAmh 231.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents