Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    መንፈሳዊ መስተንግዶ

    የቤት ሕይወታችንና ማህበራዊ ግንኙነታችን በክርስቶስ የዋህነትና ራስን ዝቅ ማድረግ የሚመራ ከሆነ እጅግ ደስተኞችና የበለጠ ጠቃሚዎች እንሆናለን፡፡ ለታይታ፣ የሌሎችን አድናቆት ለመቀስቀስ ወይም የጎብኝዎችን ቅንዓት ለማነሳሳት ከመልፋት ይልቅ በፈገግታችን፣ በርህራሄያችንና በፍቅራችን በዙሪያችን ያሉትን ሁሉ ደስተኛ ለማድረግ እንጣር፡፡ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር ለመስማማት እየጣርን መሆናችንን እንግዶች ይዩ፡፡ የእውነተኛ ክርስቲያን ቤት ከባቢ አየሩ የሰላምና የእረፍት ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነቱ ምሳሌ ውጤት የለሽ አይሆንም…፡፡MYPAmh 221.1

    ለእንግዶቻችን መጽናናትንና ደስታን ለማምጣት በምናደርገው ጥረት ለእግዚአብሔር ያለንን ግዴታ ችላ ማለት የለብንም፡፡ የጸሎት ሰዓት በማንኛውም ምክንያት ችላ መባል የለበትም፡፡ የአምልኮ ሰዓትን መደሰት እስከማትችሉ ድረስ በወሬ፣ በሳቅና በደስታ ራሳችሁን አታድክሙ፡፡ ይህንን ማድረግ ለእግዚአብሔር ሽባ መስዋዕት ማቅረብ ነው፡፡ ያለ ጥድፊያና በማስተዋል መጸለይ በምንችልበት ከምሽቱ መጀመሪያ ላይ ልመናችንን ማቅረብና ድምፆቻችንን ደስተኛ በሆነ የምሥጋና ውዳሴ ወደ ላይ ማንሳት አለብን፡፡MYPAmh 221.2

    ወደ ክርስቲያኖች ቤት ለእንግድነት የሚመጡ ሁሉ የጸሎት ሰዓት እጅግ የከበረ፣ የተቀደሰና ደስታ ያለበት ሰዓት መሆኑን ይዩ፡፡ እነዚህ የአምልኮ ጊዜያቶች በሚሳተፉባቸው ሁሉ ላይ የማጥራትንና በመንፈሳዊ ሕይወት ከፍ የማድረግ ተጽእኖ ያሳድራሉ፡፡ ለመንፈስ ሰላምን፣ እረፍትንና አመስጋኝነትን ያመጣሉ፡፡ Review and Herald, November 29, 1887.MYPAmh 221.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents