Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ያልተቀደሰ ስድ ፍቅር

    በብዙ ወጣቶች አእምሮ የጋብቻ ሃሳብ የምዋርት ኃይል ሆኖባቸዋል። ሁለት ሰዎች ይተዋወቁና በስድ ፍቅር ተይዘው ሀሳባቸው ሁሉ ይወሰዳል፣ አስተሳሰብ ይጨልማል፣ ትክክለኛ ግንዛቤ ይጠፋል። ለማንኛውም ምክርና ቁጥጥር አይገዙም። ነገር ግን ውጤቱ የፈለገው ቢሆን በራሳቸው መንገድ ይገፉበታል።MYPAmh 289.2

    የያዛቸው ስድ ፍቅር ስራውን እየሰራ ወደ ፊት እንደሚቀጥል ወረርሽኝ ወይም ተላላፊ በሽታ ሲያዩት የሚያግደው ነገር ያለ አይመስልም። እነዚህ ወጣቶች ቢጣመሩ ውጤቱ ምናልባት የሕይወት ዘመን ሐዘን እንደሚሆን የሚያስተውሉ ሰዎች አሉ። ነገር ግን እነርሱ የሚሰጡት ምክሮችና ተግሳፆች ለውጥ አያመጡም። ምናልባትም በእንደዚህ ዓይነት ህብረት ምክንያት እግዚአብሔር በግለሰቡ አገለግሎት አማካኝነት ሌሎችን የሚባርክበት ተፅእኖ የሚበላሽበት ይሆናል። ነገር ግን የተደረጉ ተማፅዕኖዎችና ውይይቶችም ተሰሚነት የላቸውም።MYPAmh 289.3

    ልምድ ያላቸው ወንዶችና ሴቶች የሚናገሩት ሁሉ ውጤት አልባ ነው። ፍላጎታቸው የሚመራቸውን ሰዎች ውሳኔ ለማስለወጥ ኃይል የለውም። በፀሎት ስብሰባዎችና ከሐይማኖት ጋር በተገናኙ ጉዳዮች ላይ ፍላጎት ያጣሉ። እርስ በርሳቸው በስድ ፍቅራቸው ስለደነቆሩ የሕይወት ተግባራት እንደ ትንሽ ነገር ተቆጥረው ችላ ተብለዋል። በየእለቱ ከእርስ በርስ ጋር ለመነጋገር የእኩለ ሌሊት ሻማን ያበራሉ። የሚያወሩት ነገር ጠቃሚና አስፈላጊነት ያለው ነገር ነውን? በፍፁም አይደለም። ነገር ግን ምንም ዋጋ የሌላቸው ከንቱ ነገሮች ናቸው።MYPAmh 289.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents