Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ለአገልግሎት መሰልጠን

    እግዚአብሔር የሰጣቸውን ብርሃን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት «ጌታ ሆይ ምን እንዳደርግልህ ትሻለህ?” የሚሉ ብዙ ወንዶችና ሴቶች ወጣቶች አለመኖራቸው አስደናቂ ነው፡፡ አንድ ወጣት ለወንጌል አገልግሎት ራሱን ካልለየ በስተቀር ለእግዚአብሔር ሥራ ራሱን ገጣሚ ለማድረግ የተለየ ጥረት አይጠበቅበትም ብሎ ማሰብ አደገኛ የሆነ ስህተት ነው፡፡ ጥሪህ ምንም ቢሆን ችሎታዎችህን ተግቶ በመማር መሻሻል አስፈላጊ ነው፡፡MYPAmh 121.1

    ወጣት ወንዶችና ሴቶች በደንብ የተገሩና የተማሩ እንዲሆኑ ከሰማይ የተላከላቸውን መልካም አጋጣሚና በረከቶችን እንዲያደንቁ ሊደፋፈሩ ይገባል፡፡ ከሁሉ የተሸለ እውቀት ማጋራትን ዓላማ አድርገው የተቋቋሙ ትምህርት ቤቶችን መልካም አጋጣሚ መጠቀም አለባቸው፡፡ ትምህርትን በመገብየት ረገድ ሰነፍና ቸልተኛ መሆን ኃጢአት ነው፡፡ ጊዜው አጭር በመሆኑና ጌታ የምድርን ታሪክ ድራማ ወደ ፍፃሜ ለማምጣት በቶሎ ስለሚመጣ ዛሬ ያሉንን መልካም አጋጣሚዎችና ዕድሎች የመጠቀም ታላቅ አስፈላጊነት አለ፡፡MYPAmh 121.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents