Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    እውነተኛ የሕይወት ፍልስፍና

    ስለ እግዚአብሔር ማንነት ግልፅ የሆነ ግንዛቤ ሲኖረንና ምን እንድንሆን እንደሚጠብቅብን መገንዘብ ወደ ምሉእ ራስን ዝቅ ማድረግ ይመራል። የተቀደሰ ቃሉን በትክክል የሚያጠና ሰው ሰብዓዊ እውቀት ሁሉን ቻይ አለመሆኑን ያውቃል። እግዚአብሔር ብቻ በሚሰጠው እርዳታ ካልሆነ በስተቀር ሰብዓዊ ብርታትና ጥበብ ደካማና ድንቁርና መሆኑን ይገነዘባል።MYPAmh 173.4

    የእግዚአብሔርን አመራር የሚከተል ሰው የሚያድን ፀጋንና የእርግጠኛ ደስታን ብቸኛ ምንጭ አግኝቷል። ያለ ኃይማኖት በእርግጠኝነት ሕይወትን በደስታ የሚመራ ሰው አይኖርም። እግዚአብሔርን መውደድ እያንዳንዱን ቅምሻችንንና ፍላጎታችንን ንፁህ ያደርጋል፣ ፍቅርን ይጨምራል፣ ተገቢ የሆነን ደስታ ሁሉ ብሩህ ያደርጋል። ሰዎች እውነት የሆነውን ነገር ሁሉ፣ መልካምና ያማረውንም ነገር ሁሉ እንዲያደንቁ ያስችላቸዋል። MYPAmh 173.5

    ከማንኛውም ነገር በላይ ለመጽሐፍ ቅዱስ ዋጋ እንድንሰጥ ሊመራን የሚገባ ነገር ቢኖር በእርሱ ውስጥ ለሰዎች የእግዚአብሔር ፈቃድ መገለጡ ነው። እዚህ ላይ የመፈጠራችንን ዓላማና ይህ ዓላማ ተፈፃሚ የሚሆንበትን መንገድ እንማራለን። የአሁኑን ሕይወት እንዴት በጥበብ ማሻሻል እንደምንችልና የወደፊት ሕይወትንም ማግኘት እንደምንችል እንማራለን። ከመጽሐፍ ቅዱስ ሌላ ማንኛውም መጽሐፍ የአእምሮን ጥያቄዎችና የልብን ናፍቆቶች ማርካት አይችልም። ሰዎች ስለ እግዚአብሔር ቃል እውቀት ሲያገኙና ለእርሱም ጆሮአቸውን ሲሰጡ እጅግ ከተዋረዱበት ዝቅ ካለ ጥልቅ አዛቅት በመውጣት የእግዚአብሔር ልጆችና ኃጢአት የለሽ መላእክት ጓደኞች ለመሆን ይነሳሉ። Counsels to Teachers, Parents an Students, P. 52 -54.MYPAmh 173.6

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents