Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    መቅደም ያለባቸውን ነገሮች ማስቀደም

    በተቀደሰ የጥምቀት ሥነ ሥርዓት የተሳተፉ ሁሉ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ባለበት በላይ ያሉትን ነገሮች ለመሻት ቃል ኪዳን ገብተዋል። ለኃጢአተኞች ደህንነት በትጋት ለመሥራትም ቃል ገብተዋል። እግዚአብሔር ስሙን የሚያነሱትን በልጁ ሞት የዳኑ ኃይሎቻችሁን እንዴት እየተጠቀማችሁ ናችሁ? ብሎ ይጠይቃቸዋል። በመንፈሳዊ መረዳት ወደ ከፍታ ለመነሳት በኃይላችሁ ሥር ያለውን ሁሉ እያደረጋችሁ ናችሁን? ፍላጎቶቻችሁንና ድርጊቶቻችሁን ከአሁኑ የዘላለማዊነት ጥያቄዎች ጋር በማጣጣም ከኃይላችሁ ሥር ያለውን ሁሉ እያደረጋችሁ ናችሁን?MYPAmh 204.4

    በእግዚአብሔር ህዝብ መካከል ተሃድሶ መኖር አለበት። “እንግዲህ ብትበሉም፣ ብትጠጡም ወይንም ማንኛውንም ነገር ብታደርጉ ሁሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት።” ጌታ የሥራውን ሸክም በላያቸው ያስቀመጠባቸው ሁሉ ባለ ማወቅ እየጠፉ ያሉ ነፍሳት ሁሉ ማስጠንቀቂያውን እንዲሰሙ መልዕክቱን ለማወጅ እየታገሉ ናቸው። ራስህን በመካድ እነርሱን በሥራቸው ለመርዳት አንድ ነገር ማድረግ አትችልምን? የተለወጣችሁ መሆናችሁን ራስ ወዳድነት በሌለው ቅንዓትና ትጋት ተነሱና አሳዩ።MYPAmh 204.5

    ነፍሳትን በማዳን ሥራ እያንዳንዱ ብር ይፈለጋል። የእግዚአብሔር ህዝብ ነን በሚሉ ሰዎች ከሰው ፊት የተሰሩ ፎቶዎችን ለማግኘት የሚውል ገንዘብ በሥራ መስክ ያሉ በርካታ ሚስዮናውያንን መርዳት ይችላል። ብዙ ትናንሽ ምንጮች ሲጠራቀሙ ትልቅ ወንዝን ይፈጥራሉ። የመጨረሻውን ማስጠንቀቂያ መልዕክት ለማወጅ ጥቅም ላይ መዋል ይችል የነበረውን ገንዘብ ለራስ ወዳድነት ደስታ ስናውለው የጌታን እቃ እያጭበረበርን ነን። የጌታን ገንዘብ ራሳችሁን ለማስደሰት የምትጠቀሙ ከሆነ እርሱ የራሱን ንብረት ለእናንተ መስጠቱን እንዲቀጥል እንዴት ትጠብቃላችሁ? እነዚያን የእርሱን ገንዘብ በራስ ወዳድነት ለፎቶግራፍ የሚያውሉ ሰዎችን ጌታ እንዴት ያያቸው ይሆን? ያ ገንዘብ ባለማወቅ ጨለማ ውስጥ ላሉ ሰዎች የሚያነቡአቸውን ነገሮች ገዝቶ ለመላክ ጥቅም ላይ መዋል ይችል ነበር።፤MYPAmh 204.6

    እግዚአብሔር የሰጠን እውነት ለዓለም መታወጅ አለበት። ይህንን ስራ የመስራት እድል ተሰጥቶናል። የእውነትን ዘር በየውኃው ዳር እንዘራለን። ጌታ ራስን መካድንና ራስን መስዋእት ማድረግን እንድንለማመድ ይጠራናል። ወንጌል ሙሉ መቀደስን ይጠይቃል። ለፎቶ ግራፍ ያለን ፍቅር በእኛ በኩል ድብቅ ምስክር የሚሆንብን ራስን የማስደሰት ተግባር ነው። በዚህ ድርጊት በመጨረሻው ቀን እሳት ለመቃጠል ብዙ እንጨት፣ ድርቆሽና ገላባ ወደ መሰረቱ መጥቷል።MYPAmh 205.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents