Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት አክብሮት መስጠት

    ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ስንመጣ በእግዚአብሔር ፊት እንዳለን እየተሰማን በአክብሮት መምጣት አለብን። አቅልሎ ማየትና ፌዝ መተው አለበት። የቃሉ አንዳንድ ክፍሎች በቀላሉ የሚስተዋሉ ቢሆኑም የሌሎች ክፍሎች እውነተኛ ትርጉም በቀላሉ የሚስተዋል አይደለም። በትዕግስት የተሞላ ጥናትና ማሰላሰል እንዲሁም ልባዊ ፀሎት መኖር አለበት። እያንዳንዱ ተማሪ ቃሉን ሲገልጥ ለመንፈስ ቅዱስ አመራር መጠየቅ አለበት:: እንደሚሰጠው የተገባው ቃል እርግጠኛ ነው።MYPAmh 171.2

    ቃሉን ለመመርመር ስትመጡ ያላችሁ መንፈስ ከጎናችሁ የሚሆኑትን የረዳት ዓይነቶች ይወስናል። ልባቸውን በማዋረድ መለኮታዊ አመራርን ከሚሹ ጋር ከብርሃን ዓለም የሚመጡ መላእክት አብረዋቸው ይሆናሉ። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ አክብሮት በጎደለው ሁኔታና በራስ ብቃት ስሜት ሲገለጥ፣ ልብ ከሁሉ አስቀድሞ የተሳሳተ ግንዛቤ የያዘ ከሆነ ሰይጣን በአጠገባቸው ይሆንና የእግዚአብሔርን ቃል ግልፅ የሆኑ ቃላት በተሳሳተ ብርሃን እንዲያዩ ያደርጋል፡፡—Testimonies to Ministers, 107-108MYPAmh 171.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents