Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የፀሎት ኃይል

    ሙሴ የእግዚአብሔር ክብር ማደሪያ የሆነውን አስደናቂ ሕንፃ አሰራር ያየው በተራራው ላይ ከእግዚአብሔር ጋር ሆኖ ነበር፡፡ እኛም እግዚአብሔር ለሰብዓዊ ዘር ያለውን ባለ ግርማ ግብ ማሰላሰል ያለብን በተራራው ላይ ከእግዚአብሔር ጋር በመሆን ነው፡፡ ለእኛ የተገባልን ተስፋ ተፈጻሚ እንዲሆንልን የባሕርይ ሕንፃችንን በዚህ መልክ እንድንሰራው እንደረጋለን፡፡ «እኔ በውስጣቸው አድራለሁ፣ ከእነርሱም ጋር እሄዳለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ፣ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ፡፡”MYPAmh 163.1

    በዕለቱ ሥራችን ላይ ተሰማርተን ሳለ በፀሎት ነፍሳችንን ወደ ሰማይ ማንሳት አለብን፡፡ እነዚህ የፀጥታ ተማጽኖዎች እንደ ዕጣን በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት ይወጣሉ፤ ጠላት ግራ ይጋባል፡፡ ልቡ በእግዚአብሔር ላይ የሚያርፍ ክርስቲያን አይሸነፍም፡፡ ማንኛውም የክፋት ጥበብ ሰላሙን ሊያጠፋ አይችልም፡፡ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ያሉ ተስፋዎች በሙሉ፣ የመለኮታዊ ፀጋ ኃይላት በሙሉ፣ የጅሆቫ ሐብቶች በሙሉ ለእርሱ ነፃ መውጣት ቃል ተገብተዋል፡፡ ሔኖክ ከእግዚአብሔር ጋር ሄደ፡፡ በእያንዳንዱ አስፈላጊ በሆነ ሰዓት በአጠገቡ ሆኖ ሊረዳው እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበር፡፡MYPAmh 163.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents