Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ከሰማያዊ ሙዚቀኞች ጋር መጣጣም

    ሰብአዊ ፍጥረቶች በመንፈስና በማስተዋል ሲዘምሩ ሰማያዊ ሙዚቀኞች መሳሪያቸውን በመውሰድ ከሰዎች ጋር የምስጋና መዝሙር ይዘምራሉ። ከእርሱ ጋር አብረን ሰራተኞች መሆን እንድንችል ስጦታዎችን ሁሉ የሰጠን አምላክ፣ አገልጋዮቹ ሁሉም ሰዎች ሊያስተውሉ በሚችሉት መልክ መናገርና መዘመር እንዲችሉ ድምፃቸውን እንዲያሰለጥኑ ይፈልግባቸዋል። የሚፈለገው ጮክ ብሎ መዘመር ሳይሆን ግልፅ የሆነ ድምፅ፣ ትክክለኛ የቃላት አጠራርና የሚሰማ ንግግር ነው። የእግዚአብሔር ምስጋና በሻካራና በጎርናና ድምፅ ሳይሆን ግልፅና ለስላሳ በሆነ ቃና መዘመር እንዲችል ድምፃቸውን ለመግራት ሁሉም ጊዜ ይውስዱ። የመዘመር ችሎታ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። ጥቅም ላይ መዋል ያለበትም ለእርሱ ክብር ነው።MYPAmh 190.4

    ስብሰባዎች በሚካሄዱበት ጊዜ በመዝሙር አገልግሎት መሳተፍ እንዲቻል አንድ መዝሙር ይመረጥ። ዝማሬውም በብልሃት በተያዙ የሙዚቃ መሳሪያዎች ይታጀብ። በስራችን ውስጥ የሙዚቃ መሳሪያ አጠቃቀምን መቃወም የለብንም። ይህ የአገልግሎት ክፍል እግዚአብሔርን በዝማሬ ማወደስ ስለሆነ በጥንቃቄ ሊመራ ይገበል።MYPAmh 190.5

    ዝማሬ ሁልጊዜ በጥቂቶች መደረግ የለበትም:: በተቻለ መጠን ጉባኤው በሙሉ አብሮ ይዘምር። Testimonies for the church, Vol. 9, P 143 -144.MYPAmh 190.6

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents