Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የሥራ በረከት

    እውነተኛ ደስታ የሚገኘው ጥሩ በመሆንና ጥሩ በማድረግ ነው፡፡ ንፁህና ከፍተኛ ደስታ የሚያገኙ ሰዎች የተሰጡአቸውን ተግባራት በታማኝነት የሚፈጽሙ ናቸው፡፡ የየዕለቱን ቀላል ተግባራት በንቀት እንዲመለከቱ የሚያደርጋቸው ተራ የሆነ ስንፍና ነው፡፡ እነዚህን ተግባራት ለማድረግ ፈቃደኛ አለመሆን አንድ ቀን በትክክል ሊታይ የሚችል የአእምሮና የግብረገብ ጉድለትን ያስከትላል፡፡ ሰነፍ ሰው በህይወቱ ዘመን በሆነ ጊዜ ውስጥ ጉድለቱ በግልጽ ይታያል፡፡ በህይወት ታሪኩ መዝገብ ላይ አምራች ያልሆነ ግን ተመጋቢ የሚሉ ቃላት ተጽፈዋል፡፡MYPAmh 139.3

    በህይወት የሥራ ዘርፎች በሙሉ ጠቃሚ የሆኑ መንፈሳዊ ትምህርቶች ይገኛሉ፡፡ መሬትን የሚያርሱ ሰዎች እያረሱ እያሉ የሚከተሉትን ቃላት ትርጉም መማር ይችላሉ፡- «እናንተ የእግዚአብሔር እርሻ ናችሁ፡፡” ሕይወት የመንፈስን መልካም ፍሬዎች እንዲያፈራ በሰብአዊ ልብ ውስጥ የእውነት ዘሮች መዘራት አለባቸው፡፡ የእግዚአብሔር በአእምሮ ውስጥ የተደረገው ማህተም ፀጋ በተሞላ ተመዛዛኝነት ይሠራዋል፡፡ ያልተገሩ የአካልም ሆኑ የአእምሮ ኃይላት ለጌታ አገልግሎት መገራት አለባቸው፡፡MYPAmh 139.4

    ክርስቶስ ለሁሉም ሰው የወንጌል አገልግሎት ሥራን ሰጥቷል፡፡ እርሱ የክብር ንጉስ ሆኖ ሳለ «የሰው ልጅ የመጣው እንዲያገለግሉት ሳይሆን ሊያገለግል ነው፡፡» ብሎ ተናግሯል፤፡ እርሱ የሰማይ ንጉስ ሆኖ ሳለ አባቱ የሰጠውን ሥራ ለመስራት ወደ ምድር ለመምጣት ተስማማ፡፡ ሥራን እጅግ አከበረው፡፡ የሥራን ክቡርነት ሊያስተምረን በመፈለግ የአናፂነት ሥራን በእጁ ሰርቷል፡፡ ከልጅነቱ ጀምሮ ቤተሰብን ለመርዳት የራሱን ድርሻ ሰርቷል፡፡ እርሱ የቤተሰብ ተቋም አካል መሆኑን በመገንዘብ የቤተሰብን ሸክም ድርሻውን በፈቃደኝነት ተሸከመ፡፡MYPAmh 139.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents