Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ኮብላዩ (የጠፋው) ልጅ

    የጠፋው ልጅ ትምህርት የተሰጠው ወጣቶችን ለማስተማር ነው። ደስታን በመፈለግና የኃጢአት ተግባራትን በመፈፀም ሕይወቱ ከአባቱ የተቀበለውን ውርስ ከሥርዓት ውጪ በሆነ አኗኗር አባከነ። በባዕድ አገር ወዳጅ የለሽ ነበር። ቡቱቶ ለብሶ፣ ተርቦ ለዓሳማ የሚሰጠውን አሰር ለመመገብ እስከ መመኘት ደረሰ። የመጨረሻ ተስፋው ተቀባይነትንና ይቅርታን ወዳገኘበትና ወደ አባቱ ልብ እንዲጠጋ ወደ ተፈቀደለት የአባቱ ቤት በመፀፀትና ራስን ዝቅ በማድረግ መመለስ ነበር። ብዙ ወጣቶች ልክ ይህ የጠፋው ልጅ እንዳደረገው ሁሉ የሕይወት ውኃ ምንጭ የሆነውን፣ የእውነተኛ ደስታ ምንጭን በመተው ለራሳቸው ውኃ መያዝ የማይችሉ ሰባራ ጉድጓዶችን በመቆፈር የግድየለሽነትን፣ ደስታን የመሻትንና የብክነትን ህይወት እየኖሩ ናቸው።MYPAmh 260.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents