Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የይስሐቅ ምሳሌ

    ማንኛውም እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው እግዚአብሔርን ከማይፈራ ሰው ጋር ያለ አንዳች አደጋ ግንኙነት አይፈጥርም። “ሁለቱ ካልተስማሙ በስተቀር አብረው መጓዝ ይችላሉን?” የጋብቻ ህብረት ደስታና ብልፅግና የሚደገፈው በሁለቱ አንድነት ነው። ነገር ግን በሚያምንና በማያምን መካከል መሠረታዊ የሆነ የዝንባሌ፣ የአመለካከትና የዓላማ ልዩነት አለ:: የሚያገለግሉት ሁለት የማይስማሙ ጌቶችን ነው:: የአንድ ሰው አቋሙ ምንም እንኳን ንፁህና ትክክለኛ ቢሆንም የማያምን ጓደኛ ተፅዕኖ የሚያምነውን ከእግዚአብሔር የማራቅ ዝንባሌ አለው።MYPAmh 294.1

    በህይወቱ ሳይለወጥ ጋብቻን የመሰረተ ሰው ካገባ በኋላ ቢለወጥ ምንም እንኳን በሐይማኖታዊ አመለካከት ሰፊ ልዩነት ቢታይባቸውም ለትዳር ጓደኛ ታማኝ የመሆን ፅኑ ግዴታ አለበት። ሆኖም የእግዚአብሔር ፈቃድ ከምድራዊ ግንኙነት በላይ መሆን አለበት። በፍቅርና በትህትና መንፈስ የሚታይ ታማኝነት የማያምነውን ጓደኛ ሊለውጥ ይችላል። ነገር ግን የሚያምኑ ሰዎች ከማያምኑት ጋር ጋብቻ መፈፀም በመጽሐፍ ቅዱስ በጥብቅ የተከለከለ ነው። “ከማያምኑ ሰዎች ጋር በአንድነት አትጠመዱ።”MYPAmh 294.2

    ይስሐቅ ዓለም የሚባረክበትን ተስፋ ወራሽ በመሆን በእግዚአብሔር በጣም የተከበረ ነበር። ሆኖም እድሜው አርባ ዓመት በነበረ ጊዜ አባቱ አብርሃም ታማኝና እግዚአብሔርን የሚፈራ ባሪያውን ጠርቶ ለልጁ ሚስት እንዲፈልግለት ባዘዘው ጊዜ ለአባቱ ውሳኔ ተገዛ። በመጽሐፍ ቅዱስ እንደተገለፀው የዚያ ጋብቻ ውጤቱ አስደሳችና ውብ ደስታ የነበረበት ነበር። “ይስሐቅም ወደ እናቱ ድንኳን አገባት፣ ርብቃንም ወሰዳት፣ ሚስትም ሆነችው፣ ወደዳትም:: ይስሐቅም ከእናቱ ሞት ተፅናና።”MYPAmh 294.3

    በይስሐቅና በዘመናችን ባሉ ወጣቶች መካከል እንዲያውም ክርስቲያን ነን በሚሉ ወጣቶች መካከል ያለው ልዩነት እንዴት የጎላ ነው! ብዙ ጊዜ ፍቅርን የመስጠት ጉዳይ በግል የሚሆን ጉዳይ ነው ይላሉ። እግዚአብሔርም ሆነ ወላጆቻቸው በምንም መንገድ ሊቆጣጠሩት የማይገባ ነገር ነው ብለው ያስባሉ። ነገር ግን ጥቂት የጋብቻ አመታት ስህተታቸውን ለማሳየት በቂ ናቸው። ነገር ግን መጥፎ ተፅዕኖውን ለማስወገድ ጊዜው አልፎበታል። ያ የጥድፊያ ምርጫ እንዲያደርጉ ያስገደዳቸው የጥበብና ራስን የመቆጣጠር እጦት የጋብቻ አንድነት ከባድ ቀንበር እስኪሆን ድረስ ክፉን እንዲያባብስ ተፈቅዶለታል።MYPAmh 294.4

    በዚህም ምክንያት ብዙዎች ለዚህ ሕይወትም ሆነ ለሚመጣው ዓለም ያላቸውን ተስፋ አጥተዋል። ከሁሉም ነገር የበለጠ በጥንቃቄ መታየት ያለበትና በእድሜ የገፉና ልምድ ያላቸውን ሰዎች ምክር የሚፈልግ ነገር ቢኖር የጋብቻ ጉዳይ ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ አማካሪነት የሚያሻውና የእግዚአብሔርን አመራር በፀሎት መጠየቅ የሚያስፈልገው ጉዳይ ቢኖር የጋብቻ ጉዳይ ነው። እግዚአብሔርንም ሆነ ሰዎችን ማማከር የሚገባው ሰዎችን የሚያስተሳስረውን እርምጃ ከመውሰድ በፊት ነው።MYPAmh 294.5

    ወላጆች ለልጆቻቸው የወደፊት ተስፋ ሃላፊነት እንዳለባቸው መዘንጋት የለባቸውም። የይስሐቅ ከአባቱ ውሳኔ ጋር መስማማት የመታዘዝን ሕይወት እንዲወድ ያስተማረው ሥልጠና ውጤት ነው። አብርሃም ልጆቹ የወላጅ ሥልጣንን እንዲያከብሩ ቢጠይቃቸውም ሥልጣኑ በራስ ወዳድነት ወይም በአምባገነንት የተነሳሳ ሳይሆን በፍቅር የተመሰረተና የእነርሱን ደስታና ደህንነት ከግምት ውስጥ ያስገባ መሆኑን የእለት ሕይወቱ ይመሰክር ነበር። MYPAmh 294.6

    አባቶችና እናቶች የልጆቻቸውን ፍቅር አቅጣጫ የማሳየትና ተስማሚ የሆኑ ጓደኞችን እንዲመርጡ የመምራት ሃላፊነት እንዳለባቸው ሊሰማቸው ይገባል። በትምህርታቸውና በህይወት ምሳሌነታቸው ከሚረዳው የእግዚአብሔር ፀጋ ጋር የልጆቻቸውን ባሕርይ ከልጅነታቸው ጀምረው ንፁህና የከበረ እንዲሆንና ጥሩና እውነት ወደ ሆነው ነገር እንዲሳቡ ባሕርያቸውን መቅረፅ ሥራቸው (ሃላፊነታቸው) እንደሆነ ሊሰማቸው ይገባል። ብጤ ብጤውን ይስባል! ብጤ ብጤውን ያደንቃል። በወጣቶች ነፍስ ውስጥ በልጅነታቸው ጊዜ የእውነት፣ የንፅህናና የበጎነት ፍቅር ከተተከለ እነዚህ ባሕርያት ያሏቸውን ወጣቶች ጓደኝነት ይሻሉ….።MYPAmh 295.1

    እውነተኛ ፍቅር በስሜት ከተነሣሣ ፍቅር በፍፁም የተለየ፣ በጣም ከፍ ያለና ቅዱስ መርህ ነው። ስሜታዊ ፍቅር ክፉኛ ሲፈተን ወዲያው ይሞታል። ወጣቶች ለራሳቸው ቤት የሚዘጋጁት በወላጆቻቸው ቤት በታማኝነት ተግባራቸውን ሲፈፅሙ ነው። በወላጆቻቸው ቤት እያሉ ራስን መካድን፣ ደግነትን፣ ሌሎችን መውደድንና ክርስቲያናዊ ርህርሄን ይለማመዱ:: ያኔ ፍቅር በልብ ውስጥ ግሎ ይቆያል። ከእንደዚህ ዓይነት ቤት የቤተሰብ ራስ ለመሆን የሚወጣ ሰው የሕይወት ጓደኛው እንድትሆንለት የመረጣትን ሴት እንዴት እንደሚያስደስታት ያውቃል። ጋብቻ የፍቅር መጨረሻ መሆኑ ቀርቶ መጀመሪያው ብቻ ይሆናል። Patriarchs and Prophets, P.174 -176.MYPAmh 295.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents