Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የዓለም ደስታ ፍቅር

    በወጣቶች አእምሮ የዓለም ፍቅር ዋና ቦታ መያዙ አስደንጋጭ ነው። እነዚህ ውድ የምህረት ሰዓታት የእግዚአብሔር ምህረት ካለመቸኮሉ የተነሣ በተለያዩ ደስታን በሚፈጥሩ ነገሮች ሁል ጊዜ ራሳቸውን እንዲያስደስቱ የተሰጡ በዓላት እንደሆኑ በመቁጠር ራሳቸውን ይመራሉ። ደስታቸውን የሚያገኙት በዓለምና በዓለም ውስጥ ባሉ ነገሮች ነው። ከዚህም የተነሣ ለሰማያዊ አባትና ለመንፈሱ ፀጋ እንግዳ ናቸው። ብዙዎች በንግግራቸው ግድ የለሾች ናቸው:: በንግግራቸው እንደሚፀድቁ ወይንም እንደሚፈረድባቸው መርሳትን ይመርጣሉ። የአብዛኞቹ ወጣቶቻችን ባህርይ በሆነው ከንቱነት፣ ባዶና ከንቱ በሆነው ንግግራቸውና ሳቃቸው እግዚአብሔር አይከብርም።MYPAmh 238.1

    ሰይጣን በዓለማዊ መደሰቻዎች ደስታን ወደ ማግኘት ሊመራቸው የተለየ ጥረት ያደርጋል። በተጨማሪም እነዚህ መደሰቻዎች ጉዳትና ክፋት የሌለባቸውና ለጤናም አስፈላጊ እንደሆኑ ለማሳየት ጥረት በማድረግ ራሳቸውን ከስህተት ነፃ እንዳያደርጉ ለማድረግ ልዩ ጥረት ያደረጋል። የቅድስናን መንገድ ከባድ በማስመሰል የዓለማዊ መደሰቻ መንገዶች አበባ የተነጠፈባቸው አስመስሎ ያቀርብላቸዋል።MYPAmh 238.2

    በውሸትና በማባበያ ቀለሞች በማስዋብ ዓለምን ከነደስታዎቹ በወጣቶች ፊት ያቀርባል። ነገር ግን የዓለም ደስታዎች ቶሎ አላቂ ናቸው። የተዘራው ሁሉ መታጨድ አለበት። ፈጣሪያችን ለሆነውና በየደቂቃው ለሚጠብቀን እግዚአብሔር የሚስቡንን ነገሮች፣ ችሎታችንን እና መክሊቶቻችንን ቀድሰን መስጠት ይበዛብናልን? ያሉን ብቃቶቻችን ለእግዚአብሔር ቀድሰን ለመስጠት እጅግ ውድ ይሆኑብናልን? MYPAmh 238.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents