Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የተጣሰ መተጫጨት

    “ቃል ገብቻለሁና አሁን ቃሌን ማጠፍ እችላለሁን?” ትዪ ይሆናል። መልሴ ይህ ነው። ከእግዚአብሔር ቃል ተቃራኒ የሆነ ቃል ገብተሽ ከሆነ በማንኛውም መንገድ ሳትዘገዪ ቶሎ ብለሽ የገበሽለትን ቃል እጠፊና ይህን የችኮላ ቃል እንድትገቢ ላደረገሽ ሞኝ ፍቅር በእግዚአብሔር ፊት ራስሽን ዝቅ በማድረግ ንሰሐ ግቢ። የዚህን ዓይነቱን መሀላ ጠብቅሽ ፈጣሪሽን ከምታዋርጂ እርሱን በመፍራት መሀላሽን ማፍረስ በጣም ይሻላል።MYPAmh 280.2

    አስታውሺ፣ ማግኘት የምትችይው ሰማይ እንዳለ ሁሉ መሸሽ ያለብሽ ወደ ጥፋት የሚወስድ የተከፈተ መንገድም አለ። እግዚአብሔር አንድን ነገር ሲል ያንኑ ማለቱም ነው። የመጀመሪያ ወላጆቻችንን ክፉንና ደጉን ከምታስታውቀው ዛፍ ፍሬ እንዳይበሉ በከለከላቸው ጊዜ አለመታዘዛቸው ዛሬ በምድራችን ላይ ላለው ዋይታ በር ከፈተ:: ከእግዚአብሔር በተቃራኒ አቅጣጫ ከተጓዝን እርሱም ከእኛ በተቃራኒ አቅጣጫ ይጓዛል። የፈለገውን ያህል ዋጋ ቢያስከፍልም ደህንነታችን የሚደገፈው እኛ ለፈቃዱ በምንሰጠው መታዘዝ ላይ ነው። ሁሉም መጨረሻ በሌለው ፍቅርና ጥበብ ተመስርተዋል። Testimonies for the Church, Vol. 5, P 361-365.MYPAmh 280.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents