Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ከእግዚአብሔር ጋር መተባበር

    እነዚህ ወጣቶች ደህንነታቸውን እየሰሩ እያሉ እግዚአብሔር በእነርሱ ውስጥ መልካም ፈቃዱን እንዲፈልጉና እንዲፈጽሙ እየሰራ ነበር። በዚህ ቦታ ነው ወደ ክንውን የሚያመሩ ሁኔታዎች የተገለፁት። የእግዚአብሔርን ፀጋ የራሳችን ለማድረግ የራሳችንን ድርሻ መፈፀም አለብን። ጌታ መፈለግንም ሆነ ማድረግን በእኛ ፈንታ ለመፈፀም ሃሳብ አይሰጠንም:: የእርሱ ፀጋ በእኛ ውስጥ ፈቃደኛ መሆንንም ሆነ ማድረግን ለመሥራት ተሰጥቶናል:: ነገር ግን በፍፁም የእኛን ጥረት እንዲተካ ተደርጎ አልተሰጠንም። ነፍሶቻችን ከእግዚአብሔር ጋር ለመተባበር መነሳሳት አለባቸው። መዳናችንን •ራሳችን እንድንሰራ መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ ይሰራል። መንፈስ ቅዱስ ሊያስተምረን እየጠራ ያለው ተግባራዊ ትምህርት ይህ ነው:: «በእናንተ ውስጥ የእርሱን መልካም ደስታ እንድትፈቅዱና እንድትፈጽሙ የሚሠራ እግዚአብሔር ነው።”MYPAmh 98.2

    እግዚአብሔር ከዳንኤልና ጓደኞቹ ጋር •እንደ ተባበረ ሁሉ ዛሬም በአገልግሎቱ ታማኝ ለመሆን ከልባቸው ከሚጥሩ ሁሉ ጋር ይተባበራል፡፡ ጥሩ የአእምሮ ችሎታና ከፍተኛ የግብረገብ ብቃት ያለው ባሕሪይ የአጋጣሚ ውጤት አይደለም። እግዚአብሔር አጋጣሚዎችን ይሰጣል። ክንውን ደግሞ እነዚህን መልካም አጋጣሚዎች በመጠቀማችን ይወሰናል። እግዚአብሔር የከፈታቸው መልካም አጋጣሚዎች በፍጥነት ተለይተው ሊታወቁና በጉጉት ሊገባባቸው ይገባል። ልክ እንደ ዳንኤል የማሸነፍን ፀጋና ሥራቸውን ለመሥራት ብርታትና ብቃት እንዲሰጣቸው በእግዚአብሔር ቢደገፉ ኖሮ ሃያል ሰዎች መሆን የሚችሉ ብዙዎች አሉ።MYPAmh 98.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents