Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ተቀባይነት ያላቸው ማህበራዊ ስብሰባዎች

    እያንዳንዱ ተፅዕኖ ማሳደር የሚችል መክሊት በቅድስና ሊጠበቅና ነፍሳትን ለክርስቶስ ለመሰብሰብ ተግባር መዋል አለበት። ወጣት ወንዶችና ሴቶች ስፖርታቸው፣ የምሽት ግብዣዎቻቸውና የሙዚቃ መዝናኛዎቻቸው በተለምዶ በሚደረጉበት ሁኔታ በክርስቶስ ተቀባይነት እንዳላቸው ማሰብ የለባቸውም።MYPAmh 250.5

    ስብሰባዎቻችን በሙሉ ፅናት ባለው መንፈሳዊ ተፅዕኖ ተለይተው መታወቅ እንዳለባቸው በተደጋጋሚ ብርሃን ተሰጥቶኛል። ወጣቶቻችን ቃሉን ለማንበብና ለማስተዋል ቢሰበሰቡና “የዘላለም ሕይወት እንዳገኝ ምን ላድርግ?” የሚለውን ጥያቄ ቢጠይቁ ኖሮ፣ ራሳቸውንም በአንድነት ከእውነት ጎን ቢያሰልፉ ኖሮ፣ ጌታ ኢየሱስ በረከቱ በልባቸው ውስጥ እንዲፈስ ይፈቅድ ነበር።MYPAmh 251.1

    እያንዳንዱ የቤተክርስቲያን አባል፣ እያንዳንዱ በተቋሞቻችን ውስጥ ያለ ሠራተኛ ይህ ሕይወት በንፅህና፣ በአስተሳሰብ ንፅህናና ከራስ ወዳድነት ነፃ በሆነ ድርጊት ረገድ በሰማይ አምላክ ፊት ለፈተና የሚዘጋጅበት ትምህርት ቤት መሆኑን መገንዘብ አለበት:: እያንዳንዱ ቃልና ተግባር፣ እያንዳንዱ አስተሳሰብ በሰማይ ባሉ የኃጢአት መመዝገቢያ መጽሐፍት ውስጥ ተመዝግቧል።MYPAmh 251.2

    በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ወደ ተቀመጠልን ወደ እውነተኛው የክብር ደረጃ መድረስና መቀደስ የምንችለው በእውነት ኃይልና መገኘት ነው። የእግዚአብሔርን መንገድ መማር የምንችለው ቃሉን እጅግ በጥንቃቄ በመታዘዝ ነው:: ቃሉን አጥኑ።” The Youth’s Instructor, August 14, 1906.MYPAmh 251.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents