Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የሚያድን ፀጋ

    ይህ ፀጋ እንዴት እንደሚገኝ አየሁ፡፡ ወደ ክፍልህ ሂድና ለብቻህ ሆነህ «እግዚአብሔር ሆይ! ንፁህ ልብ ፍጠርልኝ፤ ትክክለኛውንም መንፈስ በውስጤ አድስ” በማለት ፀልይ፡፡ ከልባችሁ ፀልዩ፡፡ ግለት ያለው ፀሎት ታላቅ ጠቀሜታ አለው፡፡ እንደ ያዕቆብ በፀሎት ታገል፡፡ አንባ፡፡ ኢየሱስ በአታክልቱ ቦታ ታላላቅ የደም ጠብታዎች አልቦታል፡፡ ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል:: ከእግዚአብሔር ብርታት ማግኘትህ እስኪሰማህ ድረስ ከክፍልህ አትውጣ፡፡ እንግዲህ ንቁ፡፡ ክፉ ፍላጎታችሁን በቁጥጥራችሁ ሥር የምታደርጉትና የእግዚአብሔር ፀጋ በእናንተ ሊታይ የሚችለው ነቅታችሁ ከፀለያችሁ ብቻ ነው፡፡MYPAmh 88.3

    እናንተን ከማስጠንቀቅ መቆጠብን ጌታ ከኔ ያርቀው፡፡ ወጣት ጓደኞቼ ሆይ! ጌታን በሙሉ ልባችሁ እሹ፡፡ በልባዊ ቅናት ወደ እርሱ ኑ፡፡ ያለ እግዚአብሔር እርዳታ እንደምትጠፉ ከልባችሁ ከተሰማችሁ፣ ዋሊያ ወደ ውሃ ምንጮች እንደምትናፍቅ እርሱን ከተጠማችሁ፣ ያኔ ጌታ በፍጥነት ያጠነክራችኋል፡፡ ያኔ ሰላማችሁ ከማስተዋል ሁሉ ይበልጣል፡፡ ደህንነትን የምትጠብቁ ከሆነ መፀለይ አለባችሁ፡፡ ጊዜ ውሰዱ፡፡ በፀሎቶቻችሁ የምትጣደፉና ግድ የለሾች አትሁኑ፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ በእናንተ እንዲኖርና በዓለም ውስጥ እንደ መብረቶች እንድታበሩ እግዚአብሔር በእናንተ ውስጥ የተሟላ ለውጥን እንዲያደርግ ለምኑት፡፡ ለእግዚአብሔር ሥራ እንቅፋቶች ወይንም እርግማን አትሁኑ፡፡ ለሥራው ድጋፍና በረከት መሆን ትችላላችሁ፡፡ ደህንነትን በሙላትና በነፃ መደሰት እንደማትችሉ ሰይጣን ይነግራችኋልን? ከሆነም አትመኑት፡፡MYPAmh 88.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents