Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ፈተና ኃጢአት ለመሥራት ምክንያት አይደለም

    እግዚአብሔርን እናመልካለን የሚሉ መንፈሳቸውን የመጠበቅና እጅግ በሚረብሹ ሁኔታዎች ውስጥ እንኳን ራሳቸውን የመግዛት እጅግ የተቀደሰ ግዴታ አለባቸው:: በሙሴ ላይ አርፈው የነበሩ ሸክሞች (ሐላፊነቶች) በጣም ትልቅ ነበሩ፡፡ እንደ እርሱ ከባድ ፈተና የሚፈተኑ በጣም ጥቂቶች ናቸው፡፡ ነገር ግን ይህ ኃጢአት ለመስራት ዋስትና ሊሆን አይችልም፡፡ እግዚአብሐየር ለህዝቡ በቂ የሆነ ዝግጅት አድርጓል፡፡ በእርሱ ብርታት የሚደገፉ ከሆኑ የሁኔታዎች መጫወቻ አይሆኑም፡፡ ነፍስ እንድትሸከመው የመጣው ፈተና የፈለገውን ያህል ታላቅ ቢሆንም ኃጢአት መስራት ግን የራሳችን ምርጫ ነው፡፡MYPAmh 47.1

    ምድራዊውም ሆነ የገሃነም ኃይሎች ማንንም ሰው ኃጢአት እንዲሰራ የማስገደድ ሥልጣን የላቸውም፡፡ ሰይጣን በደካማ ጎኖቻቸን በኩል ጥቃት ይሰነዝርብናል፤ ነገር ግን መሸነፍ የለብንም፡፡ ጥቃቱ የፈለገውን ያህል ከባድ ወይም ያልተጠበቀ ቢሆንም እግዚአብሔር እርዳታውን ስለ ሰጠን በእርሱ ብርታት አሸናፊዎች እንሆናለን፡፡ Patriarchs and Prophets p. 421MYPAmh 47.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents