Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የአእምሮ ሰካራሞች

    የአነቃቂና ስሜትን የሚያነሳሱ ታሪኮች ፍላጎት እያደገ ሲሄድ የግብረ ገብ ፍላጎት እየታዛባ ይሄድና አእምሮ ይህንን ቆሻሻና ያልተሟላ ምግብ ካልተመገበ በቀር እርካታ አያገኝም። አንድ አዲስ ልበ- ወለድ ወይም የታሪክ ወረቀት በእጃቸው ከሌለ በስተቀር በእርግጠኝነት ደስተኛ መሆን የማይችሉ የክርስቶስ ተከታይ ነኝ ባይ ወጣት ሴቶችን አይቻለሁ። ሰካራም ሰው አስካሪ መጠጥን እንደሚናፍቅ አእምሮአቸው ከእነዚህ መጻሕፍት ለሚገኝ መነቃቃት ይናፍቃል። እነዚህ ወጣቶች ራስን ቀድሶ የመስጠትን መንፈስ አላሳዩም። ጓደኞቻቸውን ወደ ሕይወት ውኃ ምንጭ ሊመራ የሚችል ሰማያዊ ብርሃን በላያቸው አልበራም። ጥልቅ የሆነ መንፈሳዊ ልምምድ የላቸውም:: ሁልጊዜ የዚህ ዓይነቱ ንባብ በፊታቸው ባይሆን ኖሮ ለመታደስ የሚያበቃ ጥቂት ተስፋ ሊኖራቸው ይችል ነበር። ነገር ግን ስለሚናፍቁት ያንኑ ያገኙታል።MYPAmh 183.2

    በዚህ ሕይወት የሚኖራቸውን ጠቃሚነት እያበላሹ ያሉትንና በሰማይ ማህበረሰብ ውስጥ ያለውን ዘላለማዊ ሕይወት እንዲያገኙ የሚያስችላቸውን ልምምድ ሳያገኙ እየቀሩ ያሉትን ወጣት ወንዶችና ሴቶችን በማየቴ አዝኛለሁ። ለእነዚህ ሰዎች “የአእምሮ ሰካራሞች” ከሚል ስም የተሻለ ገጣሚ ስም ማግኘት አንችልም።MYPAmh 183.3

    በማንበብ መሻትን አለመግዛት ልክ በምግብና በመጠጥ መሻትን አለመግዛት በአእምሮ ላይ የሚያሳድረውን ያህል ጎጂ ተፅእኖ ያሳድራል።MYPAmh 183.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents