Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    እጅግ ከፍ ያለ ውስጣዊ ማነሳሻ

    ለእኛ እግዚአብሔርን የማክበር ፍላጎት ለድርጊት ከሚያነሳሱን ከሁሉም ምክንያቶች እጅግ ኃይለኛው ምክንያት መሆን አለበት። የእግዚአብሔርን እቃዎች እንዴት በጥበብ መጠቀም እንዳለብን እንድናስተውልና የተሰጡንን እድሎችና አጋጣሚዎች ለማሻሻል ማድረግ የሚገባንን ጥረት ሁሉ ማድረግ እንድንችል ሊመራን ይገባል። የአካል ጥንካሬያችንና የአእምሮ ግልፅነታችን ታማኝ መጋቢዎች ሊያደርጉን እንዲችሉ አእምሮን፣ አጥንትን፣ ጡንቻንና ነርቭን እጅግ ጤናማ በሆነ ሁኔታ መጠበቅ እንድንችል ሊመራን ይገባል። የራስ ወዳድነት ፍላጎት ሥራውን እንዲሰራ ቦታ ቢሰጠው አእምሮን ያቀጭጫል! ልብንም ያጠነክራል። የራስ ወዳድነት ፍላጎት እንዲቆጣጠረን ከተፈቀደለት የግብረገብ ኃይልን ያጠፋል። ከዚያ በኋላ ተስፋ መቁረጥ ይመጣል።MYPAmh 99.4

    እውነተኛ ስኬት ለወንዶችና ሴቶች የሚሰጠው ለዳንኤል ስኬትን ከሰጠ አምላክ ነው። የዳንኤልን ልብ ያነበበው አምላክ በደስታ የባሪያውን ንፅህናና በውስጡ ያለውን ተነሳሽነት እንደዚሁም እግዚአብሔርን ለማክበር ያለውን ቁርጥ ውሳኔ አየ። በሕይወታቸው የእግዚአብሔርን ዓላማ የሚፈጽሙ ሁሉ የተሰጣቸውን ተግባር ለመፈፀም ራሳቸውን በቅርበትና በፅናት በሥራው ውስጥ በማስቀመጥ ልፋትን የሚጠይቅ ጥረት ማድረግ አለባቸው። The Youth’s Instructor, August 20,1903MYPAmh 99.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents