Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የየእለቱ ተግባራት

    ልጆች የየእለቱን ቀላል ተግባራት እንዲፈጽሙአቸው እግዚአብሔር እንዳስቀመጠላቸው አድርገው እንዲቆጥሩ ትምህርት ተሰጥቷቸው ቢሆን ኖሮ፣ ታማኝነት ውጤታማ አገልግሎትን ለመስጠት የሚሰለጥኑበት ትምህርት ቤት እንደሆነ ቢማሩ ኖሮ ስራቸው ምን ያህል ያማረና የከበረ በሆነ ነበር። እያንዳንዱን ሥራ ለእግዚአብሔር እንደምንሰራ አድርገን መሥራት ዝቅተኛ በሆነ ሥራ ላይ እንኳን ውበትን ያለብሰውና በምድር ላይ ያሉ ሰራተኞችን በሰማይ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ከሚፈጽሙ ቅዱሳን ፍጡራን ጋር ያቆራኛል።MYPAmh 213.2

    ልክ መልአክት ከፍ ባለው ቦታ በታማኝነት ሥራቸውን እንደሚያከናውኑ ሁሉ እኛም በተመደብንበት የሥራ ቦታዎቻችን በታማኝነት ማከናወን አለብን። የእግዚአብሔር አገልጋዮች እንደሆኑ የሚሰማቸው ሁሉ የትም ቦታ እምነት የሚጣልባቸው ሰዎች መሆን አለባቸው። የሰማይ ዜጎች ከሁሉ የተሻሉ ምድራዊ ዜጎችም ናቸው። ለእግዚአብሔር ሥራ ያለን ትክክለኛ አመለካከት ለመሰሎቻችን ስላለን ኃላፊነትም የጠራ እይታ እንዲኖረን ይመራል።MYPAmh 213.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents