Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምክርን አለመቀበል

    የዚህ ዓይነት ማግባትና መጋባት ልዩ ከሆኑ የሰይጣን መሳሪያዎቸ አንዱ በመሆኑ ሰይጣን ሁል ጊዜ እቅዱ ይሳካለታል። በዚህ ጉዳይ ላይ ጓደኛሞች ለምክር ሲመጡ በጣም አስጨናቂ የሆነ ረዳት የለሽነት ስሜት ይሰማኛል። እግዚአብሔር እንድናገር የፈቀዳቸውን ቃላት እነግራቸዋለሁ። ነገር ግን በእያንዳንዱ ነጥብ ላይ ጥያቄ እያነሱ የራሳቸውን ፈቃድ ለመፈፀም ለጥበብ ይለምናሉ።MYPAmh 290.2

    የራሳቸውን ፍላጎትና ዝንባሌ የማሸነፍ ኃይል ስለሌላቸው ለአደጋ የተጋለጠ ጋብቻ ይፈጽማሉ። ራሳቸውን በእግዚአብሔር እጅ ትተው በጥንቃቄና በፀሎት ጉዳዩን አይመለከቱም። የእግዚአብሔር ፍርሃት ዓይናቸው ፊት አይታይም። ከሰው ምክርም ሆነ ከእግዚአብሔር ጥበብ ሳይኖራቸው ሁሉንም ነገር በትክክል ያስተዋሉ ይመስላቸዋል::MYPAmh 290.3

    ጊዜው ካለፈ በኋላ ስህተት መፈፀማቸውንና በዚህ ሕይወት ደስታቸውንና የነፍሳቸውን መዳን አደጋ ላይ መጣላቸውን ይረዳሉ። ስለ ጉዳዩ ከራሳቸው በስተቀር ማንም ሌላ ሰው እንደሚያውቅ መቀበል አይፈልጉም። ምክርን ተቀብለው ቢሆን ኖሮ ወደ ፊት የሚያሳልፏቸውን የስጋትና የሐዘን ዓመታትን ማምለጥ ይችሉ ነበር። የራሳቸውን መንገድ መከተል የሚፈልጉ ምክርን ጥለውታል። ትክክለኛ የህሊና ግንዛቤና ፍርድ ጣልቃ ሊገቡ የሚችሉትን እያንዳንዱን ገደብ ስሜት ተሸክሞ ያሻግራቸዋል።MYPAmh 290.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents