Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ዓለማዊ ጓደኝነትን አለመቀበል

    ወጣቶች ዓላማቸውና የህይወት ሥራቸው ምን መሆን እንዳለበት በአፅንኦት ማሰብና ልምዶቻቸው ከክፋት እርኩሰት የፀዳ እንዲሆን የሚረዳቸውን መሠረት መጣል አለባቸው። በሌሎች ላይ ተፅእኖ ለማሳደር በራስ የሚተማመኑ መሆን አለባቸው። በባህር ላይ የሚያድጉ ሊሊዎች ሥሮቻቸውን በላይ ካለው አልፎ ወደ ጥልቅ በመስደድ ቀዳዳ ባለው ግንዳቸው አማኝነት ለእድገት አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን በመሳብ እንከን የለሽ አበባዎቻቸውን በባህር ሆድ ላይ እንዲታይ ወደ ብርሃን ያመጣሉ። ይህ ተክል እንከን የለሽ ውበቱን የሚያበላሽ ወይም የሚያጎድፍ ነገርን ሁሉ አይቀበልም።MYPAmh 269.1

    ከእነዚህ ሊሊዎች ትምህርት በመውሰድ ምንም እንኳን ግብረ ገብን በሚያረክሱና ነፍስን በሚያጠፉ ነገሮች የተከበብን ብንሆንም እነዚህን መጥፎ ተፅእኖዎች በመቋቋም ራሳችንን ክፉ ጓደኝነት ልባችንን ሊያበላሽ በማይችልበት ቦታ ማስቀመጥ እንችላለን:: ወጣቶች በየግላቸው ወደ ላይ በሚወስደው መንገድ ላይ ሳይደናቀፉ ከሚሄዱ ጋር ጓደኝነት ለመፍጠር መሻት አለባቸው:: ለመርህ እውነተኛ እንደሆኑ ሰዎች እያንዳንዱን ክፉ ተፅእኖ ከሚቀበሉ ጋር እና ትጉህ ካልሆኑና ከፍ ያለ ባሕርይ እንዲኖራቸው ከማይሹ ጋር፣ እምነት ሊጣልባቸው ከማይችሉ ጋር ጓደኝነት ከመፍጠር መራቅ አለባቸው። ወጣቶች እግዚአብሔርን ከሚወዱና ከሚፈሩ ጋር ጓደኝነት ይፍጠሩ። እነዚህ የከበሩና ፅኑ ባሕርያት በሐይቅ ሆድ ውስጥ ንፁህ አበባን በሚያፈካ የሊሊ አበባ ይመሰላሉ። አዋራጅ የሆኑ ተፅእኖዎችን በፅኑ ይቃወማሉ! ለራሳቸው ንፁህና የከበረ ባሕርይን ለማሳደግ የሚረዳ ነገር ብቻ ይሰበስባሉ። በመለኮታዊ ቅርፅ ለመቀረፅ የሚሹ ናቸው።l.—The Youth’s Instructor, January 5, 1893.MYPAmh 269.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents