Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ከሙሉ ልብ አገልግሉ

    አንድ ግለሰብ በዕለታዊ ሕይወቱ የሚገልፀው መንፈስና መርሆዎች በሕይወት ሁሉ የሚገለፁ ናቸው፡፡ የተወሰነ ሥራ በመሥራት የተወሰነ ደሞዝ ማግኘት የሚፈልጉና ከሁኔታዎች ጋር ራሳቸውን ለማስማማት ወይንም ለመማር ሳይጨነቁ ገጣሚዎች ሆነው መገኘት የሚመኙ ሰዎች እግዚአብሔር በስራው ውስጥ ድርሻ እንዲኖራቸው የሚጠራቸው አይደሉም፡፡ የአካል፣ የአእምሮና የሞራል ኃይላቸውን እንዴት መቆጠብ እንዳለባቸው የሚማሩ፣ እግዚአብሔር በረከቱን አትረፍርፎ ሊያፈስላቸው የሚችል ሠራተኞች አይደሉም፡፡ ምሳሌነታቸው ተዛማች ነው፡፡ የሚገዛቸው ዓላማ የራስ ፍላጎት ነው፡፡ ቁጥጥር የሚያስፈልጋቸውና የተነገራቸውን ብቻ የሚሠሩ ሰዎች መልካምና ታማኝ ባርያ ለመባል የሚበቁ አይደሉም፡፡ መሠራት የሚያስፈልገውን ማንኛውንም ነገር ለማድረግ ፈቃደኛ የሆኑና ጥረትን፣ ታማኝነትንና ትጋትን የሚገልፁ ሠራተኞች ይፈለጋሉ፡፡MYPAmh 126.7

    ብዙዎች ብቃት የለሽ የሚሆኑት ባይሳካልኝስ በሚል ሰበብ ኃላፊነትን ስለሚሸሹ ነው፡፡ በመሆኑም ከልምድ የሚገኝ ትምህርትን ሳያገኙ ይቀራሉ፡፡ ይህንን ትምህርት ማንበብ፣ መጥናትና ሌሎችም እድሎች ሊያስገኙ የማይችሉት ነው፡፡MYPAmh 127.1

    ሰው ሁኔታዎችን ለመለወጥ ይችላል፤ ነገር ግን ሁኔታዎች ሰውን እንዲቀይሩ መፈቀድ የለባቸውም፡፡ ሁኔታዎችን ለሥራ እንደሚያስፈልጉ መሣሪያዎች እንቁጠራቸው፡፡ እኛ ልንቆጣጠራቸው ይገባል፤ እነርሱ ግን እንዲቆጣጠሩን መፍቀድ የለብንም፡፡MYPAmh 127.2

    ኃይል ያላቸው ሰዎች ተቃውሞ የደደረሰባቸው፣ ግራ መጋባት የገጠማቸውና ዓላማቸው የተጨናገፈባቸው ናቸው፡፡ ያላቸውን ኃይል በተግባር ላይ ካዋሉ የገጠሙአቸው መሰናክሎች በረከት ይሆኑላቸዋል፡፡ በራስ መተማመንን ያገኛሉ፡፡ ግጭትና ግራ መጋባት በእግዚአብሔር መተማመንን እንዲለማመዱና ኃይልን የሚጨምር ጽናት እንዲያሳድጉ ያደርጋል፡፡ The Ministry of Healing, P. 498-500.MYPAmh 127.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents