Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ለአገልግሎት ማብቃት

    ለእግዚአብሔር ለመስራት እየጣሩ ያሉና ለሌሎች ለማካፈል እንዲችሉ ለራሳቸወ ለማግኘት ተግተው የሚሹ የብርሃን ማስተላለፊያ መስመሮች ለመሆን ያለማቋረጥ ከእግዚአብሔር ብርሃንን ይቀበላሉ፡፡ ወጣቶቻችን ልክ እንደ ዳንኤል ልምዶቻቸውን፣ የምግብ ፍላጎቶቻቸውንና ሌሎች ከፍተኛ ስሜቶቻቸውን ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር ቢያስማሙ ኖሮ ራሳቸውን ከፍ ላለ ስራ ብቁ ያደርጉ ነበር፡፡ ከአእምሮአቸው ርካሽና የማይረቡ ነገሮችን ማስወገድ አለባቸው፡፡ የማይጠቅሙና ስጋዊ ደስታ የመፈለግ ማንነቶች የእግዚአብሔርን ልጅ ስጋ በመብላትና ደሙን በመጠጣት በእርሱ በማመን ከሚኖሩ ሰዎች ሕይወትና ልምምድ ያለ ቦታው እንዳለ ነገር መወገድ አለባቸው፡፡MYPAmh 34.3

    ምንም እንኳን የመማር ዕድሎች በሙሉ ባጠገባቸው ቢኖሩም በእግዚአብሔር የአትክልት ቦታ ለመስራት የሚያበቃቸውን ትምህርት ሳያገኙ መቅረት ሊኖር እንደሚችል መገንዘብ አለባቸው፡፡ የሚፈለግባቸው ብቃትና ማስተዋል ያለበት መሰጠት ሳይኖር በእግዚአብሔር አገልግሎት ውስጥ መሰማራት አይችሉም፡፡ ለከበረና ከፍ ላለ ተግባር መጠናከር ያለበትን ውድ አእምሮ ለደስታና ራስን ለማዝናናት ከሰጡ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ኃይሎች ዝቅ ያደርጉና የተሰጡአቸውን መክሊቶች በጥበብ ባለመጠቀማቸው ምክንያት በእርሱ ፊት በደለኞች ይሆናሉ፡፡ MYPAmh 34.4

    የእነርሱ የቀጨጨ መንፈሳዊነት ለእግዚአብሔር ያስጠላዋል፡፡ አብረዋቸው የሚሆኑ ሰዎችን አእምሮ ያጎድፉታል፤ ያረክሱታልም፡፡ በቃላቶቻቸውና በድርጊቶቻቸው ለተቀደሱ ነገሮች ግድ የለሽ መሆንን ወይም ትኩረት አለመስጠትን ያደፋፍራሉ፡፡ በዚህ ድርጊታቸው የራሳቸውን ነፍስ ብቻ አደጋ ላይ የሚጥሉ ሳይሆን ምሳሌነታቸውም ከእነርሱ ጋር ግንኙነት ላላቸው ሁሉ ጎጂ ነው፡፡ ክርስቶስን ለመወከል ሙሉ በሙሉ ብቃት የላቸውም:: የኃጢአት ባሪያዎች፣ ግድ የለሾች፣ ሃላፊነት የጎደላቸውና ሞኞች ከእርሱ እየራቁ ይሄዳሉ፡፡MYPAmh 34.5

    በአነስተኛ ስኬቶች የሚረኩ ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር አብረው ሰራተኞች ለመሆን አይበቁም፡፡ በጥንቃቄ ካልተጠበቁ በቀር አእምሮ አቅጣጫን መሳት በሚችልበት ቦታ ሁሉ እንዲስት ለማድረግና ሌሎች ነፍሳትን ለማሳት በሰራዊቱ ውስጥ እንዲሰለጥኑ ለማድረግ ሰይጣን ሃሳቦችን ያቀርባል፡፡ እምነት እንዳላቸው ሊገልፁ ወይም የአምልኮ መልክ ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ካላቸው ፍቅር ይልቅ ደስታን አፍቃሪዎች ናቸው፡፡MYPAmh 34.6

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents