Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ንቁ፣ፀልዩም

    ውድ ወጣቶች ወይ! የጠላት ፈተናዎች በማንኛውም መልኩ ቢመጡ ለመቋቋም እንድትችሉ ፀጋና ብርታት እንዲሰጣችሁ ቀኑን ስትጀምሩ ወደ ኢየሱስ ከልባችሁ መፀለይን ቸል አትበሉ:: በእምነትና ነፍሳችሁን በማስጨነቅ ተግታችሁ ከፀለያችሁ ጌታ ፀሎታችሁን ይሰማል። ነገር ግን መንቃትና መፀለይ ይገባችኋል:: ኢየሱስ እንዲህ ብሏል:- “ጠይቁ ይሰጣችኋል፤እሹ ታገኙማላችሁ፤መዝጊያን አንኳኩ ይከፈትላችሁማል። የሚጠይቅ ይቀበላል፣ የሚሻ ያገኛል፣ በር የሚያንኳኳም ይከፈትለታል። ከእናንተ ማንኛው ሰው ነው ልጁ እንጀራ ቢጠይቀው ድንጋይ የሚሰጥ? ወይም ዓሳ ቢጠይቅ እባብ የሚሰጥ አለን? እናንተ ክፉ ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ሥጦታን መስጠት ካወቃችሁ በሰማይ ያለው አባታችሁ ለሚጠይቁት እንዴት አብዝቶ መልካም ሥጦታን አይሰጣቸውም? ”MYPAmh 83.1

    ልጆችና ወጣቶች ከነሸክማቸውና ግራ መጋባታቸው ወደ ኢየሱስ መምጣትና እርሱ ልመናቸውን እንደሚያከብርና የሚፈሉጉትን ነገር እንደሚሰጣቸው ማወቅ ይችላሉ። ከውስጥህ ፍላጎት ያለህ ሁን፤ በውሳኔህ የፀናህ ሁን። የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን በማቅረብ ያለጥርጥር እመን:: እግዚአብሔር መልስ እንደሚመልስ ከማሰብህ በፊት የተለየ ስሜት እንዲሰማህ አትጠብቅ:: ከእርሱ የምትጠይቀውን ነገር እንደምትቀበል ከማመንህ በፊት እግዚአብሔር ለአንተ መስራት ያለበትን የተለየ መንገድ አትቀይስ። ነገር ግን በእርሱ ታመንና ፀሎትህን እግዚአብሔር እንደሚያከብረው በሙሉ እምነት በመቀበል የፀሎትህ መልስ በትክክለኛው ጊዜና የሰማዩ አባትህ ለአንተ መልካም እንደሆነ በሚያየው መንገድ እንደሚመጣልህ በማመን ሁሉንም ነገር በጌታ እጆች ተው:: በየዋህነት ሂድ፤ ወደ ፊት መጓዝህን ቀጥል።MYPAmh 83.2

    “እግዚአብሔር አምላክህ ፀሐይና ጋሻህ ነውና እርሱም ፀጋና ግርማ ይሰጥሃል:: በፊቱ በቅንነት የሚሄዱትን መልካም ነገርን አያሳጣቸውም።” መዝ፡ 84፡11MYPAmh 83.3

    “እናንተ ቅዱሳን እግዚአብሔርን ፍሩት፣ የሚፈሩት አንዳችን አያጡምና:: የአንበሳ ደቦሎች ደኸዩ፣ ተራቡም፤ እግዚአብሔርን የሚፈልጉት ግን ከመልካም ነገር ሁሉ አይጎድሉም።” መዝ34፡9-10MYPAmh 83.4

    “አንደበትህን ከክፉ ከልክል ከንፈሮችህንም ሽንገላን ከመናገር። ከክፉ ሽሽ መልካምንም አድርግ፣ ሰላምን እሻ ተከተላትም:: የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደ ጻድቃን ጆሮቹም ወደ ጩሃታቸው ናቸውና። መታሰቢያቸውን ከምድር ያጠፋ ዘንድ የእግዚአብሔር ፊት ክፉን በሚያደርጉ ላይ ነው። ጻድቃን ጮሁ፣ እግዚአብሔርም ሰማቸው ከመከራቸውም ሁሉ አዳናቸው። እግዚአብሔር ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው፤ መንፈሳቸው የተሰበረውንም ያድናቸዋል።” መዝ 34፡13-18MYPAmh 83.5

    ክፉ ማድረግን ብንተውና መልካም ማድረግን ብንማር ሊሰጡን ቃል የተገቡ እጅግ ብዙና የበለፀጉ ተስፋዎች እዚህ አሉልን። ዮሴፍ፣ ሙሴና ዳንኤል እንዳደረጉት ሁሉ ዓላማችሁን ከፍ ባለው ሕይወት ላይ አድርጉ። ባሕሪይን መገንባት የሚያስካፍለውን ዋጋ ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ባሕሪያችሁን ለአሁንና ለዘላለም ገንቡ።MYPAmh 83.6

    እኛ ደካሞችና ጥበብ የሌለን ነን። ነገር ግን እግዚአብሔር እንዲህ ብሏል፡- “ከእናንተ ማንም ጥበብ ቢጎድለው ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፣ እርሱም ይሰጠዋል።” ያዕ፡ 1፡5 ብቻ ፍፁም ለመሆን፣ እጆችህ እግዚአብሔርን እንዲያውቁ፣ በአገልገሎት ለመቆየት ብትማር በበጉ ደምMYPAmh 83.7

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents