Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    መጽሐፍ ቅዱስ ታላቁ መምህር

    አእምሮአችን እንዲያተኩርበት በተቀደሰ የእግዚአብሔር ቃል ውስጥ የቀረቡልን ትምህርቶች ምንድር ናቸው? ማሰላሰልን የሚጠይቅ ከፍ ያለ ነገር ያለው የት ነው? በጣም ደስ የሚሉ አሳቦች የት ናቸው? የሰብዓዊ ሳይንስ ምርምሮች በትክክለኛነታቸውና ምስጢራዊነታቸው በምን መልክ ነው ከመጽሐፍ ቅዱስ ሳይንስ ጋር የሚነፃፀሩት? የዚህን ያህል ጥልቅና ልባዊ የሆነ አሳብ ውስጥ ያለ የእውቀት ጥንካሬን የሚሻ ማንኛውም ነገር የት ነው ያለው?MYPAmh 167.5

    እንዲናገረን የምንፈቅድለት ከሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ማንኛውም ነገር ሊያስተምረን የማይችለውን ነገር ያስተምረናል፡፡ ነገር ግን ያሳዝናል! ሰዎች ከእግዚአብሔር ቃል ይልቅ በሌሎች ነገሮች ላይ ትኩረት አድርገዋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የተቀደሱ የእውነት ሐብቶችን በሙሉ ይዞ በጠረጴዛዎቻችን ላይ ተጋድሞ እያለ ዋጋ ቢስ ሥነ-ጽሁፎችና ልበ-ወለድ ታሪኮች በስስት እየተነበቡ ናቸው፡፡ ቅዱስ ቃሉ የሕይወት ደንብ ቢደረግ ኖሮ ያጠራል፣ ከፍ ያደርጋል፣ ይቀድሳልም፡፡ ቃሉ ለሰው የተላከ የእግዚአብሔር ድምፅ ነው፤ እናዳምጠዋለንን?MYPAmh 168.1

    «ቃልህ ሲነበብ ብርሐን ይሰጣል፤ ለትሁታንም ማስተዋልን ይሰጣል፡፡» አእምሮን ለማንቃትና ለማብራት መላእክት ቃሉን በሚመረምሩ ሰዎች አጠገብ ይቆማሉ፡፡ የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ለመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርት የዛሬ አንድ ሺህ ስምንት መቶ ዓመት ገደማ በመጣላቸው ተመሳሳይ ኃይል ለእኛም ይመጣልናል፡፡ «መጽሐፍትን እሹ፤ በእነርሱ የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታስባላችሁ፣ እነርሱ ስለ እኔ የሚናገሩ ናቸው፡፡” Review & Herald, Jan. 11, 1881.MYPAmh 168.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents