Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ጤናና ራስን መግዛት

    በወጣቶች ውስጥ ንጹህና የከበረ ባሕርይ እንዲኖራቸው ለማድረግ የምግብ ፍላጎታቸውን እንዲቆጣጠሩ ብርታት ለመስጠትና ራስን ከሚያዋርዱ እንቅስቃሴዎች ለመታቀብ ከሚረዱ ታላላቅ ነገሮች አንዱ የተሟላ የአካል ጤንነት ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ እነዚህ ራስን የመግዛት ልምዶች ራሳቸው ጤንነትን ለመጠበቅ አስፈላጊ ናቸው፡፡MYPAmh 152.3

    ወንዶችና ሴቶች ስለ ሰው ሕይወት ሳይንስና ጤንነትን እንዴት ማግኘትና መጠበቅ እንደሚቻል መማር ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ በተለይ ወጣቶች በሕይወት ውስጥ በየዕለቱ ሥራ ላይ የሚውል እውቀትን የሚያካብቱበት ወቅት አሁን ነው፡፡ ወጣቶች መልካም ልምዶችን ለመመሥረት፣ በሂደት ያገኙአቸውን መጥፎ ልምዶች የማረም፣ ራስን የመግዛትን ኃይል የማግኘትና አጥብቆ የመያዝ፣ እቅድ የማውጣት፣ እንደዚሁም የሕይወት ተግባራትን በሙሉ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋርና ከሌሎች መሰል ፍጡሮች ደህንነት አንጻር ራስን ከተግባር ጋር የማለማመድ ወቅት አሁን ነው፡፡ ኢየሱስ የአካል ጥያቄዎችን ችላ አላለም፡፡ MYPAmh 152.4

    ለሰዎች የአካል ሁኔታ አክብሮት ስለነበረው የታመሙትን በመፈወስና የአካል ክፍሎቻቸውን ላጡ እየመለሰላቸው ይዘዋወር ነበር፡፡MYPAmh 152.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents