Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የአለባበስ ተጽእኖ

    በአለባበስ አምሮ መገኘትን አንቃወምም፡፡ ትክክለኛ ውበት መናቅም ሆነ መወገዝ የለበትም፡፡ እምነታችን በትክክል ሥራ ላይ ከዋለ ከሌሎች ልዩ ሆነን እንታይና አለባበሳችን ቀላል ሆኖ ለመልካም ሥራ የምንቀና እንሆናለን፡፡ ነገር ግን በአለባበሳችን ሥርዓትንና አምሮ መገኛትን ስናጣ እውነትን በግልጽ እንተዋለን፡፡ ምክንያቱም እውነት ሰውን ከፍ ከፍ ያደርጋል እንጂ አያዋርድም፡፡ አማኞች ስለ አለባበሳቸው ግድ የለሾች ሲሆኑና በባህርያቸው ያልተሞረዱና ሸካራዎች ሲሆኑ የእነርሱ ተጽእኖ እውነትን ይጎዳል። በእግዚአብሔር መንፈስ የተመራው ሐዋሪያ “እኛ ለዓለም፣ ለመላእክትና ለሰዎች የምንታይ ነን” ብሏል። የክርስቶስ ተከታዮች ነን የሚሉ ሁሉ በዓለም ላይ እያሳደሩ ያሉትን የየእለቱን ተፅዕኖዎች ሰማይ እየመዘገባቸው ነው…።MYPAmh 229.1

    ቀለል ያለ አለባበስ ነገሮችን ማገናዘብ የምትችልን ሴት የበለጠ ተመራጭ ያደርጋታል። ስለ አንዳንድ ሰው ባህርይ በሚለብሰው የአለባበስ አይነት ፍርድ እንሰጣለን። የተስተካከለ ባሕርይና በደንብ የተኮተከተ አእምሮ ቀለል ያለና ገጣሚ የሆነ ልብስ በመምረጥ ይገለጣል። ከፋሽን ባርነት የተላቀቀች ወጣት ሴት የህብረተሰብ ጌጥ ነች። በአለባበስዋና በባሕርይዋ ትሁትና የማታስመስል እውነተኛ ሴት የምትገለፀው ባላት የሞራል ብቃት መሆኑን ማስተዋልዋን ታሳያለች:: በውበቱ ከሜዳ አበባዎች ጋር የሚነፃፀረው ቀለል ያለ አለባበስ እንዴት የሚያምርና ደስ የሚል ነው! Review and Herald November 17, 1904. MYPAmh 229.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents