Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የአርቲስቶች አርቲስት/የሰዓሊዎች ሰዓሊ/

    እግዚአብሔር አእምሮኣችንን ለመሳብና ፍላጎት እንዲኖረን ለማድረግ ዙሪያችንን በተፈጥሮ ውብ ነገሮች ከቧል። የተፈጥሮ ግርማዎችን ከእርሱ ባህሪይ ጋር እንድናዛምድ እቅዱ ነው። የተፈጥሮ መጽሐፍን በታማኝነት ብናጠና ኖሮ ስለ ዘላለማዊው ፍቅሩና ኃይሉ ለማሰላሰል ፍሬያማ ምንጭ እናገኝ ነበር።MYPAmh 237.3

    በጨርቅ ላይ የሚያማምሩ ቅቦችን የሚሰራውን የሰዓሊን ሥራ ብዙዎች ያደንቃሉ። የብዙዎች ያላቸው ኃይል በሙሉ ለስዕል ሥራ የዋለ ቢሆንም ስራዎቻቸው ግን ከተፈጥሮው እጅግ በጣም የራቁ ናቸው፡፡ ሥነ ሥዕል በተፈጥሮ ውስጥ የሚታየውን ፍፅምና በፍፁም ሊደርስ አይችልም። ብዙ ክርስቲያኖች የምሽቱን የፀሐይ ጥልቀት የሚገልፅ ሥዕል ሲያዩ እጅግ ይደሰታሉ። የሰዓሊውን ችሎታ ያመልካሉ። ነገር ግን በግርማ የተሞላውን እውነተኛውን ፀሐይ ደመና በሌለባቸው ምሽቶች ሁሉ የማየትን እድል በቸልታ ያልፉታል።MYPAmh 237.4

    ሰዓሊው ንድፉን ያገኘው ከየት ነው? ከተፈጥሮ ነው። ነገር ግን ታላቁ የሰዓሊዎች ሰዓሊ ተለዋዋጭ በሆነው በሰማይ ጨርቅ ላይ በግርማ የተሞላውን የፀሐይ ግባት ስሏል። የሰማይን ነፃብራቆች እንድናይና በውስጡ ያለውን ግርማ አእምሮአችን እንዲያስተውል በማለት በላይ ያሉት የሰማይ ደጆች የተከፈቱ ይመስል እግዚአብሔር ሰማያትን በወርቅ፣ በብርና በቀይ ቀለሞች ለብጦታል። ብዙዎች በግድየለሽነት ይህንን ሰማይ የሳለውን ስዕል እንዳያዩ ፊታቸውን ያዞራሉ። በሰማያት በሚታዩት ብልጫ ባላቸው ቁንጅናዎች ዘላለማዊ የሆነውን የእግዚአብሔርን ፍቅርና ኃይል ማየት ይሳናቸዋል። ነገር ግን የሰዓሊዎች ሰዓሊን በመኮረጅ የተሰሩ ጉድለት ያላቸውን ቅቦች ሲያዩና ሲያመልኩ እጅግ ይደሰታሉ። Review and Herald, July 25,1871.MYPAmh 237.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents