Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ሐይማኖትን ሥራችን እናድርገው

    ሐይማኖት የህይወት ትልቁ ሥራ መሆን አለበት። ሁሉም ነገር ለዚህ ተገዥ መሆን አለበት። የነፍስ፣ የአካልና የመንፈስ ኃይሎች በሙሉ በክርስቲያናዊ ጦርነት ላይ መሠማራት አለባቸው። ለጥንካሬና ለፀጋ ክርስቶስን መመልከት አለብን። ያን ጊዜ ኢየሱስ ለእኛ በርግጠኝነት እንደሞተልን ሁሉ የምናገኘው ድልም እርግጠኛ ይሆናል።MYPAmh 77.1

    ወደ ክርስቶስ መስቀል መቅረብ አለብን። መማር ያለብን የመጀመሪያው የሰላም ትምህርት በመስቀል ግርጌ ለኃጢአታችን መናዘዝ ነው። የክርስቶስን ፍቅር ሙሉ በሙሉ ማስተዋል የሚችል ማነው? እናት ለልጅዋ ካላት ፍቅር የበለጠ ለዘላለም ርህሩህና ለራስ የሞተ ነው። የሰውን ነፍስ ዋጋ ማወቅ ከፈለግን በሕያው እምነት መስቀሉን መመልከትና ለዳኑት የዘላለም ሳይንስና ዝማሬ የሆነውን ማጥናት መጀመር አለብን። የጊዜያችንና የመክሊታችን ዋጋ ሊገመት የሚችለው ለደህንነታችን በተከፈለልን መስዋዕትነት ታላቅነት ብቻ ነው። ለእግዚአብሔር የሚገባውን ፍቅራችንንና አገልግሎታችንን በመንፈግ እያሳየን ያለነው ምን አይነት ምስጋና ቢሲነት ነው! ሁሉን መስዋዕት ላደረገልን ጌታ ራሳችንን መስጠት ይበዛልን? “እኔ አሸንፌ ከአባቴ ጋር በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጥሁ ለአሸናፊዎች ከኔ ጋር በዙፋኔ ላይ እንዲቀመጡ እሰጣቸዋለሁ::” እያለ ክርስቶስ ዘላለማዊ ክብርን እየሰጠን ሳለ እኛ የዓለምን ወዳጅነት መምረጥ እንችላለንን?MYPAmh 77.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents