Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 47 - ክርስቲያናዊ ትምህርት

    ለዘላለም ህይወት የሚያዘጋጅ ትምህርት ሰብዓዊ አእምሮ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ነገር ነው፡፡ ለእግዚአብሔር የተሰጠ ህይወት የድንቁርና ህይወት መሆን የለበትም፡፡ ኢየሱስ ወንጌልን እንዲሰብኩ ያልተማሩ ዓሣ አጥማጆችን ስለመረጠ ብዙዎች በትምህርት ላይ የተቃውሞ ድምፅ ያሰማሉ፡፡ ኢየሱስ ወዳልተማሩት እንዳደላ አፅንተው ይናገራሉ፡፡ ብዙ የተማሩና የተከበሩ ሰዎች ትምህርቱን አመኑ፡፡ እነዚህ ያለፍርሃት ህሊናቸው ላመነው ነገር ቢታዘዙ ኖሮ ኢየሱስን ይከተሉት ነበር፡፡ ፈቃደኛ ቢሆኑ ኖር ችሎታዎቻቸው ተቀባይነትን ያገኙና በክርስቶስ አገልግሎቶች ላይ ይውሉ ነበር፡፡ ነገር ግን ፊታቸውን በሚየኮሳትሩ ካህናትና ቀናተኛ በሆኑ ገዢዎች ፊት በክርስቶስ እንደሚያምኑ በመናገር ከዚህ ትሁት ገሊላዊ ጋር ባላቸው ግንኙነት ዝናቸውን አደጋ ላይ ለመጣል የሞራል ኃይል አልነበራቸውም፡፡MYPAmh 112.1

    የሁሉን ልብ የሚያውቅ ይህንን አስተዋለ፡፡ የተማሩና የተከበሩ ሰዎች ሊያደርጉት ብቃት እያላቸው ሥራውን ካልሰሩ ሥራውን ለመሥራት ታዛዥና ታማኝ የሆኑትን ይመርጣል፡፡ እርሱ ከምድር ሲሄድ በምድር ላይ ያለውን ሥራ ወደፊት እንዲቀጥሉ ያልተማሩ ሰዎችን መርጦ ከራሱ ጋር አገናኛቸውና አስተማራቸው፡፡MYPAmh 112.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents