Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ሌሎችን ለማዳን ማህበራዊ ግንኙነት መፍጠር

    ክርስቶስ ራሱን ከሰብኣዊ ዘር ፍላጎቶች ጋር የማገናኘት ምሳሌ የሆነውን ቃሉን የሚሰብኩና የጸጋውን ወንጌል የሚቀበሉ ሁሉ ሊከተሉት የሚገባቸው ምሳሌ ነው። እኛ ማህበራዊ ግንኙነቶችን የምንቃወም አይደለንም። ራሳችንን ከሌሎች መለየት የለብንም። ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች ለመድረስ እነርሱ ወዳሉበት ሄደን ልናገኛቸው ይገባል። ብዙ ጊዜ በራሳቸው ስምምነት ላይፈልጉ ይችላሉ። የሰዎች ልቦች በመለኮታዊ እውነት ሊነካ የሚችለው ከመድረክ ላይ ቆሞ በመስበክ ብቻ አይደለም:: ምንም እንኳን ዝቅተኛ ቢመስልም ልክ እንደ ስብከቱ ሁሉ የሰዎችን ልብ መድረስ የሚቻልበት ሌላ የሥራ መስክ አለ።እርሱም ዝቅተኛ በሆኑ ሰዎች ቤትና በታላላቅ ሰዎች መኖሪያ ነው! በመስተንግዶ ጠረጴዛና ክፋት በሌለባቸው ለደስታ በሚደረጉ የስብሰባ ቦታዎች ነው።MYPAmh 258.1

    የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት እንደ መሆናችን ደስታን ለመፈለግ ብቻ በማለት ከአለማውያን ከንቱነት ጋር ለመተባበር ከዓለም ጋር አንቀላቀልም:: እንደ እነዚህ ዓይነት ግንኙነቶች ውጤታቸው ጉዳት ብቻ ነው። በቃላቶቻችንም ሆነ በተግባራችን፣ በዝምታችን ወይም በቦታው በመገኘታችን ለኃጢአት በፍፁም እውቅና መስጠት የለብንም። የትም ብንሄድ ክርስቶስን ይዘን መሄድና የአዳኙን ክቡርነት ለሌሎች መግለጥ አለብን። ነገር ግን ሃይማኖታቸውን በድንጋይ ግንብ ውስጥ በመደበቅ ሊያቆዩት የሚሞክሩ ሰዎች መልካም ማድረግ የሚችሉበትን ውድ አጋጣሚዎች ያጣሉ። በማህበራዊ ግንኙነት አማካኝነት ክርስትና ዓለምን መድረስ ይችላል። መለኮታዊ ብርሃንን ያገኘ እያንዳንዱ ግለሰብ የሕይወትን ብርሃን ያላገኙ ሰዎችን መንገድ ማብራት አለበት።MYPAmh 258.2

    ሁላችንም የኢየሱስ ምስክሮች መሆን አለብን። ማህበራዊ ኃይል በክርስቶስ ፀጋ በመቀደስ ነፍሳትን ወደ አዳኙ ለማምጣት ጥቅም ላይ መዋል አለበት። እኛ በራስ ወዳድነት በራሳችን ፍላጎቶች ብቻ የተመሰጥን ሳንሆን ሌሎች የእኛን በረከቶችና መልካም እድሎች እንዲካፈሉ የምንሻ መሆናችንን ዓለም ይይ። የእኛ ሐይማኖት ርህራሄ የሌለንና ከሌሎች የምንፈልግ እንድንሆን እንደማያደርገን ማየት አለባቸው።ክርስቶስን አግኝተናል የሚሉ ሁሉ እርሱ ለሰው ጥቅም እንዳገለገለ ማገልገል አለባቸው።MYPAmh 258.3

    ክርስቲያኖች ለዓለም ፊታቸው የጨለመና ደስታ የራቃቸው ሕዝቦች እንደሆኑ የሚገልፅ የተሳሳተ ስዕል በፍፁም መስጠት የለብንም። ዓይኖቻችን በኢየሱስ ላይ ቢያተኩሩ ኖሮ ርህሩህ አዳኝን እንመለከትና ከፊቱ ላይ ብርሃን እንቀበላለን። የእርሱ መንፈስ በነገሰበት ሁሉ በዚያ ሰላም ይገኛል። እዚያ ፀጥ ያለ በእግዚአብሔር ላይ ቅዱስ መታመን ስላለ ደስታም ይኖራል።MYPAmh 258.4

    ተከታዮቹ ምንም እንኳን ሰብአዊ ቢሆኑ የመለኮታዊው ባሕርይ ተካፋዮች መሆናቸውን ሲያሳዩ ክርስቶስ ይደሰታል። እነርሱ ሀውልቶች ሳይሆኑ ሕይወት ያላቸው ወንዶችና ሴቶች ናቸው። ልቦቻቸው በመለኮታዊ ፀጋ ጤዛ በመታደስ ወደ ጽድቅ ፀሐይ ይከፈታሉ! ይሰፋሉም። በእነርሱ ላይ የሚበራውን ብርሃን በክርስቶስ ፍቅር በሚበራ ስራ ወደ ሌሎች ያንፀባርቃሉ። The Desire of Ages, P. 152-153.MYPAmh 258.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents