Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ፀሎት አምባችን

    በእነዚህ የመጨረሻ ቀናት አደጋዎች መካከል ወጣቶች በደህንነት መጠበቅ የሚችሉት ሁልጊዜ እየጨመረ በሚሄድ ነቅቶ መጠበቅና ፀሎት ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል በማንበብና በፀሎት ሰዓት ደስታን የሚያገኝ ወጣት ከሕይወት ምንጭ በሚመጣ በረከት ሁልጊዜ ይታደሳል፡፡ እጅግ ከፍ ወዳለው የግብረገብ ብቃትና ሌሎች ሊያስቡበት ከሚችሉት በላይ ወደ ሆነው የአስተሳሰብ ስፋት ይደርሳል፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት መፍጠር መልካም አሳቦችን፣ የከበሩ ግቦችን፣ እውነትን አጥርቶ ማየትንና ከፍ ያሉ የተግባር ዓላማዎችን ያደፋፍራል፡፡ ስለዚህ ራሳቸውን ከእግዚአብሔር ጋር የሚያገናኙ የእርሱ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ተደርገው ተቆጥረዋል፡፡ እነዚህን ጌታ በዓለም የብርሃንና የጥበብ መተላለፊያ እስኪያደርጋቸው ድረስ ስለ እግዚአብሔርና የዘላለም ሕይወት የጠራ ግንዛቤ እያገኙ ያለማቋረጥ ከፍ ከፍ እያሉ ይሄዳሉ፡፡MYPAmh 162.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents