Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ከሁሉ አነስተኛ በሆነው ታማኝ መሆን

    “ከሁሉ ትንሽ በሆነው የታመነ በብዙም የታመነ ይሆናል።” MYPAmh 95.1

    ሕይወትን ስኬታማ የሚያደርገው ዓለም ‹ትንሽ ነገሮች› ለሚላቸው ተገቢውን ትኩረት መስጠት ነው። ትንንሽ የበጎ አድራጎት ተግባሮች፣ ትናንሽ ራስን የመካድ ድርጊቶች፣ ጠቃሚ የሆኑ ቀላል ቃላትን መናገር፣ ከትናንሽ ኃጢአቶች መጠንቀቅ-ክርስትና ማለት ይህ ነው። ለየእለቱ በረከቶች አመስጋኝ መሆን፣ በየዕለቱ የሚገጥሙንን ዕድሎች በጥበብ ማሻሻል፣ የተሰጡንን መክሊቶች በትጋት መንከባከብ- ጌታ እየጠራን ያለው ለዚህ ነው። MYPAmh 95.2

    ትናንሽ ተግባራትን በታማኝነት የሚፈጽም ሰው የታላላቅ ኃላፊነቶችን ጥያቄ ለመመለስ የተዘጋጀ ይሆናል። በዕለታዊ ሕይወቱ ደግና ትሁት የሆነ ሰው፣ በቤተሰቡ ውስጥ ለጋስና ታጋሽ የሆነ ሰው፣ የሁል ጊዜ ዓላማው ቤቱን ደስተኛ ማድረግ የሆነ ሰው፣ ራሱን ለመካድና ጌታ ሲጠራው መስዋዕትነትን ለመክፈል የመጀመሪያው ሰው ይሆናል። ሰው “በልቡ እንዳሚያስብ እንደዚሁ ነው።” ብዙ ሐሳቦች የአንድን ቀን ያልጠፈ ታሪክ ይመሰርታሉ፡፡MYPAmh 95.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents