Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ልበ - ወለድ መጽሐፍትን የማንበብ ውጤቶች

    በዚህ መንገድ እንዲያድጉ የተደረጉ ልጆችን አይቻለሁ:: እነዚህ ልጆች በአገራቸውም ሆነ በውጭ አገር እረፍት የለሾች ወይም የሚያልሙና እጅግ ተራ የሆኑ ነገሮችን ካልሆነ በስተቀር መናገር የማይችሉ ናቸው። ከፍ ያሉ ነገሮችን ለመሻት የተፈጠሩ ክቡር የአካል ክፍሎች፣ ባለቤቱ በማይረቡ ርዕሰ ጉዳዮች እስኪረካና ማንኛውንም ከፍ ያለ ነገር የመድረስ ኃይል እስኪያጣ ድረስ፣ ተራ ወደ ሆኑ ወይም ተራ ከሆኑቱ የከፉ ነገሮችን ወደ ማሰላሰል ደረጃ ዝቅ ብለዋል። መንፈሳዊ አስተሳሰብና ንግግር ጣዕም የለሽ ሆኖባቸዋል።MYPAmh 182.3

    አስተሳሰብ የሚመራ ነው። የዘላላማዊው ሕይወት ተስፋዎቻችን ማዕከል የሆነውን የክርስቶስን እውቀት የማግኘት እድሎችን ችላ በማለት እጅግ ብዙ ነገርን እያጡ ያሉ ነፍሳትን በማየቴ ልባዊ የሆነ ሐዘኔታ ይሰማኛል። እውነተኛውን እግዚአብሔርን የመምሰል ምሳሌን ማጥናት ይችሉበት የነበረው ብዙ ውድ ጊዜ ባክኗል።MYPAmh 182.4

    የተሳሳተ የንባብ ልምዶችን በማዳበራቸው ምክንያት ጤናማ የሆነ የአእምሮ አሰራራቸውን ያጡ እኔ በግሌ የማውቃቸው አንዳንድ ሰዎች አሉ። ትናንሽ አለመግባባቶችን እያነሱ በታመመ አስተሳሰብ ሕይወትን ይመራሉ። ጤናማና ማገናዘብ የሚችል አእምሮ የማያያቸው ነገሮች ለእነርሱ ሊሸከሙኣቸው ከሚችሉት በላይ የሆኑ ፈተናዎችና ሊታለፉ የማይችሉ እንቅፋቶች ይሆኑባቸዋል። ለእነርሱ ሕይወት የማያቋርጥ ጥላ ነው።MYPAmh 182.5

    ስሜትን የሚያነቃቁ ታሪኮችን ለማንበብ የመሽቀዳደም ልምድን ያዳበሩ ሰዎች የአእምሮ ጥንካሬያቸውን ሽባ በማድረግ ራሳቸውን ንቁ ለሆነ አስተሳብና ምርምር ብቁ እንዳይሆን እያደረጉ ነው። ተግባራዊ ክርስቲያን የመሆን ጥረት ሁሉ በምኞት ብቻ ያበቃል። በእንደዚህ አይነት ስነ-ጽሁፍ አእምሮአቸውን እየመገቡ እያሉ እውነተኛ ክርስቶስን የሚመስሉ መሆን አይችሉም።MYPAmh 182.6

    በልጅነት ጊዜ የተመሰረቱ ልምዶች እነርሱ ሲያድጉ አብረው አድገው ከጥንካሬያቸው ጋር አብረው ጠንክረዋል። እነዚህን ልምዶች ለማሸነፍ ያደረጉአቸው ጥረቶች ምንም እንኳን በቁርጠኝነት የተደረጉም ቢሆን ስኬታማ የሆኑት በከፊል ነው።MYPAmh 182.7

    በአካል ላይ ያለው ውጤትም አደገኛነቱ ከዚህ ያነሰ አይደለም። ይህንን ስነ-ጽሁፍ ለማንበብ ካለው ፍላጎት የተነሳ የነርቮች ስርኣት አላስፈላጊ የስራ ጫና ተፈጥሮበታል ። በአንዳንድ ሁኔታዎች ወጣቶችና በእድሜ የበሰሉትም ቢሆኑ ያለመጠን ከማንበብ የተነሳ በሽባነት በሽታ ተሳቃይተዋል። በቀላሉ ሊጎዳ የሚችል የአእምሮ ፋብሪካ ደክሞ መስራት እስኪያቅተው ድርስ በማያቋርጥ መነቃቃት ሁኔታ ውስጥ ከመቆያቱ የተነሳ ሽባነትን አስከትሏል።MYPAmh 183.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents