Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የአብሮ አደጎች ተጽዕኖ

    ከወላጆቻቸው እይታ ውጭ የሆኑና ቤታቸውን የተዉ ወጣቶች ጓደኞቻቸውን እንዲከተሉ በከፍተኛ ሁኔታ ተትተዋል። እነዚህ ወጣቶች ማስታወስ ያለባቸው ነገር ቢኖር የሰማዩ አባታቸው ዓይን በእነርሱ ላይ መሆኑንና እያንዳንዱን የሚያስፈልጋቸውን ነገርና እያንዳንዱን ፈተና እንደሚያይ ነው። በትምህርት ቤቶች ራሳቸው በመረጡት የተግባር አቅጣጫ ምክንያት አእምሮአቸው ዝቅተኛ በሆነ ቅርፅ የተቀረፀ መሆኑን ይገልፃሉ፡፡ በልጅነት ጊዜ ጥበብ በጎደለው ሥልጠና ምክንያት ወደ አንድ አቅጣጫ ያጋደለ ባሕርይን አጎልብተዋል:: እድሜያቸው እየገፋ በሄደ ቁጥር እነዚህ ጉድለቶች ልምምዳቸውን ለማበላሸት በእነርሱ ውስጥ ቀርተዋል። በቃልና በሕይወት ምሳሌነት በግብረገብ ኃይል ደካማ የሆኑትን በስህተት አቅጣጫ ይመሩአቸዋል።MYPAmh 108.4

    ውድ ወጣቶች! ጊዜ ወርቃማ ነው። እንክርዳድ እየዘራችሁ ነፍሶቻችሁን ለአደጋ አታጋልጡ። የምትመርጡአቸውን ጓደኞች በተመለከተ ግድ የለሽ መሆን የሚያስከፍላችሁ ዋጋ ከምትችሉት በላይ ነው። በሌሎች ባሕርይ ውስጥ የከበረውን ነገር እዩ። እነዚህ ባህሪያት ክፉን ለመቋቋምና መልካምን ለመምረጥ የሞራል ኃይል ይሆኑአችኋል። ኢላማችሁን ከፍ ባለ ቦታ አድርጉ። እግዚአብሔርን የሚወዱና የሚፈሩ መምህራንና ወላጆች ቀንና ማታ በፀሎታቸው ሊከተሉአችሁና ሊያስጠነቅቁአችሁም ይችላሉ። እናንተ መጥፎ ጓደኞችን የምትመርጡ ከሆነ ይህ ሁሉ ጥረት ከንቱ ይሆናል። ምንም ዓይነት ግልፅ አደጋ የማታዩና እንደ ምርጫችሁ ክፉውንም ሆነ መልካሙን ማድረግ የምትችሉ እንደሆነ የሚሰማችሁ ከሆነ የኃጢአት እርሾ በአደገኛ ሁኔታ አእምሮአችሁን እያጎደፈውና እያረከሰው እንደሆነ መለየት አትችሉም፡፡MYPAmh 108.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents