Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የሚባክን ጊዜ የለም

    ወጣት ወንዶችና ሴቶች ሆይ፣ የምታባክኑት ጊዜ የላችሁም:: በፀባይ ግንባታችሁ ላይ ጠንካራ ጣውላዎችን ለማምጣት ከልባችሁ ፈልጉ:: ስለ ክርስቶስ ብለን ታማኞች እንድትሆኑ እንለምናችኋለን። ዘመኑን ለመዋጀት እሹ። በየቀኑ ለእግዚአብኼር አገልግሎት ራሳችሁን ቀድሱ:: ይህንን ማድረግ ስትጀምሩ ያለ ስራ የምታሳልፉዋቸው ብዙ የበዓል ቀናትና የራሳችሁን ፍላጎት ለማርካት ብዙ ገንዘብ እንደማያስፈልጋችሁ ትገነዘባላችሁ። ሰማይ ለመሻሻልና በክርስቶስ አምሳል ለመቀረፅ የሚሹ ሰዎችን እየፈለገ ነው። ሰብዓዊ ወኪል ራሱን ለክርስቶስ አሳልፎ ሲሰጥ መንፈስ ቅዱስ ለእርሱ ብዙ ነገሮችን ይፈጽምለታል።MYPAmh 195.4

    እያንዳንዱ እራሱን መስዋእት የሚያደርግ እውነተኛ የእግዚአብሔር ሰራተኛ ለሌሎች ሲል ያለውን ሁሉ ሊሰዋና ራሱም ሊሰዋ ዝግጁ ነው። ክርስቶስ እንዲህ ይላል:- “ነፍሱን የሚወድ ያጠፋታል፣ የዚህን ዓለም ሕይወት የጠላ ለዘላለማዊ ሕይወት ያቆያታል።” እውነተኛ የሆነ ክርስቲያን እርዳታ በሚያስፈልግበት ቦታ እርዳታ ለማድረግ ልባዊ የሆነና በደንብ የታሰበበት ጥረት በማድረግ ለእግዚአብሔርና ለመሰሎቹ ያለውን ፍቅር ያሳያል። በአገልግሎት ላይ እያለ ሕይወቱን ሊያጣ ይችላል፣ ነገር ግን ክርስቶስ እንቁዎችን ወደ ራሱ ለመሰብሰብ በሚመጣበት ጊዜ መልሶ ያገኘዋል። The youth’s Instructor, September 10, 1907MYPAmh 195.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents