Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የመንፈሳዊነት እጦት ተገለጠ

    እንደዚህ ዓይነት ግለትና መነሳሳት ሰማያዊ መሰረት የሌለው ነው። ሙሉ በሙሉ ምድራዊ ነው። ክርስቶስ ብዙ ነገር ያደረገላቸውን ሰዎች ዝንጉነት የሰማይ መላእክት በሀዘኔታ ይመለከታሉ። ራሳቸውን ለማስደሰት ብቻ ወደ ኖሩ ሰዎች ህመምና ሞት ሲመጣ ጊዜ ካለፈባቸው በኋላ በማሰሮአቸው ዘይት እንደሌላቸውና የህይወት ታሪካቸውን ለመደምደም በፍፁም ገጣሚ አለመሆናቸውን ይገነዘባሉ።MYPAmh 249.3

    በብዙ ማህበራዊ ስበሰባዎች ላይ የሚደረጉ ንግግሮች መንፈስ፣ በልብ ውስጥ ያለው ምን እንደሆነ ይገልጣሉ። ለማሳቅ ተብለው የሚወሩ ከንቱ ንግግሮችና የሞኝነት ፈሊጦች ክርስቶስን በትክክል አይወክሉትም። እነዚህን ቃላት የሚናገሩ ሰዎች ቃላቶቻቸው በሰማይ መዝገብ ተመዝግበው ያሉ ሲሆን በቃላቶቻቸው ምክንያት የሚመጣባቸውን ፍርድ ለመጋፈጥ ፈቃደኞች አይሆኑም። እነርሱን በሚያዳምጡ ሰዎች አእምሮ መጥፎ አሻራ የተቀመጠ ከመሆኑም በላይ በክርስቶስ ላይ ነቀፌታን አምጥተዋል። እነሆ ወጣቶች ቃላቶቻቸውን በደንብ መቆጣጠር ቢችሉ ኖሮ እንዴት መልካም ነበር! ምክንያቱም ከቃላቶቻቸው የተነሣ ይጸድቃሉ ወይም ይፈረድባቸዋል፡፡ ክርስቶስ ድርጊታችሁን እየተመለከተና ንግግራችሁን እያዳመጠ በሄዳችሁበት ሁሉ በአጠገባችሁ እንዳለ አስታውሱ። ሲናገራችሁ ድምፁን ለመስማት ታፍራላችሁን? ንግግራችሁን እንደሚሰማ ስታውቁስ ታፍራላችሁን?...MYPAmh 249.4

    አንድ ጊዜ ልባዊ ክርስቲያን የነበረና አሁን በዓለማዊ መደሰቻዎች ላይ የሚሳተፍ ሰው በአደገኛ ሁኔታ ውስጥ ነው። አስፈላጊ በሆነ ሰማያዊ ከባቢ አየር የተሞላውን ቦታ ትቶ ጭጋግና ውርጭ ወዳለበት ከባቢ አየር ውስጥ ተዘፍቋል። በብዙ ሁኔታዎች የደስታ ግብዣዎችና ለመደሰቻ ተብለው የሚደረጉ ስብሰባዎች ለክርስቶስ ኃይማኖት መሰደቢያ ናቸው።MYPAmh 249.5

    ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን ግንኙነት በልቡ የሚጠብቅ ሰው በእነዚህ ነገሮች አይሳተፍም። የሚሰማቸው ቃላት የከነዓን ቋንቋ ስላይደሉ የሚጥሙት አይደሉም። ተናጋሪዎቹ በልባቸው ለእግዚአብሔር መልካም ጣእመ ዜማ ለማሰማታቸው ምንም ማረጋገጫ አይሰጡም።MYPAmh 249.6

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents