Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    በፀሎት ላይ ያለን አመለካከት

    በጉባኤም ሆነ በግል የአምልኮ ጊዜ ልመናችንን ለጌታ ስናቀርብ በጉልበታችን ተንበርክከን የመጸለይ ዕድል አለን፡፡ ምሳሌያችን የሆነው ኢየሱስ «ተንበርክኮ ጸለየ፡፡” ስለ ደቀ መዛሙርቱም «ተንበርክከው ፀለዩ” ተብሎ ተጽፏል፡፡ ጳውሎስም «ጉልበቶቼን ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ አባት አንበረክካለሁ» ብሏል፡፡ እዝራም የእሥራኤልን ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት ሲናዘዝ በጉልበቱ ተንበርክኳል፡፡ ዳንኤልም «በቀን ሦሥት ጊዜ በጉልበቱ በመንበርከክ ፀለየ፤ በአምላኩም ፊት ምስጋና ሰጠ፡፡”MYPAmh 164.1

    ለእግዚአብሔር የሚሰጥ እውነተኛ አክብሮት የእርሱን መገኘትና ዘላለማዊ ታላቅነቱን ከመገንዘብ የመነጨ ነው፡፡ የዚህ የማይታይ አምላክ መኖር ሲሰማን እያንዳንዱ ልብ በጥልቅ መነካት አለበት፡፡ እግዚአብሔር በዚያ ስላለ የፀሎት ሰዓትና ቦታ የተቀደሱ ናቸው፡፡ አክብሮት በአመለካከትና በባሕርይ የሚገለጽ እንደመሆኑ ይህንን የሚፈጥር ስሜት እየጨመረ ይሄዳል፡፡ ባለመዝሙሩ ዳዊት «ስምህ ክቡርና ቅዱስ ነው» ይላል፡፡ መላእክት ይህንን ስም ሲያነሱ ፊታቸውን ይሸፍናሉ፡፡ ታዲያ እኛ የወደቅንና ኃጢአተኞች የሆንን ይህንን ስም በከንፈራችን ስናነሣ እንዴት ባለ አክብሮት ማድረግ ይገባን ይሆን!MYPAmh 164.2

    እግዚአብሔር የሚገኝበት ቦታ እንዴት ባለ አክብሮት መታየት እንዳለበት መጽሐፍ ቅዱስ በሚገልጸው ቃላት ላይ በደንብ ማሰብ ለወጣቶችና ለአዛውንት መልካም ነው፡፡ «ጫማህን ከእግርህ አውልቅ የቆምክበት ቦታ የተቀደሰ ነውና” በማለት ከሚነደው ቁጥቋጦ ውስጥ ሙሴን አዘዘው፡፡ ያዕቆብ የመላእክቱን ራዕይ ካየ በኋላ «ጌታ በዚህ ስፍራ ነው፣ እኔም አላወቅኩም ነበር…» በማለት ተናግሮ ነበር፡፡ Gospel Workers, P. 178-179.MYPAmh 164.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents