Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ትርፍራፊውን መሰብሰብ

    ውድ እህቶቼ ሆይ የአለባበስ ሁኔታችሁን በመጽሐፍ ቅዱስ ከተሰጡት ህጎች ጋር ብታጣጥሙት ኖሮ ደሃ እህቶቻችሁን የምትረዱበት እጅግ ብዙ ነገር ይኖራችሁ ነበር። ገንዘብ ብቻ ሳይሆን ጊዜም ይኖራችኋል:: አብዛኛውን ጊዜ ይህ በጣም ይፈለጋል። እናንተ በአስተያየታችሁ፣ በብልሃቶቻችሁና በሙያችሁ ልትረዷቸው የምትችሏቸው ብዙዎች አሉ። ቀላል ሆኖ የሚስብ አለባበስን አሳዩአቸው። ብዙ ሴቶች ከእግዚአብሔር ቤት የሚርቁበት ምክንያት የራሳቸውን መናኛና የማይገጥም ልብስን ከሌሎች ሴቶች ልብስ ጋር በማወዳደር ነው። ከዚህ ንፅፅር የተነሳ በቀላሉ የሚነካ መንፈስ ያላቸው ብዙዎች መራር የሆነ የበታችነትና ኢፍትሃዊነት ስሜት ይሰማቸዋል። ከዚህም የተነሳ ብዙዎች የኃይማኖትን እርግጠኝነት በመጠራጠር ልባቸውን ለወንጌል ወደ ማደንደን ተመርተዋል።MYPAmh 206.6

    ኢየሱስ “ምንም ነገር እንዳይባክን ትርፍራፊውን ሰብስቡ” ይለናል። በየቀኑ በሺዎች የሚቆጠሩ በረሃብ፣ በደም መፍሰስ፣ በቃጠሎና በመቅሰፍቶች እየጠፉ እያሉ የሰው ዘር ወዳድ የሆነ ሁሉ መሰሎቹን ለመጥቀም ምንም ነገር እንዳይባክንና አላስፈላጊ ወጪ እንዳይሆን መጠበቅ አለበት።MYPAmh 206.7

    ጊዜያችንንም ሆነ አስተሳሰባችንን ማባከን ስህተት ነው:: ለራሳችን ክብር የምንሰዋትን እያንዳንዷን ደቂቃ እያበከንናት ነን። እያንዳንዷ ደቂቃ ዋጋ ቢሰጣትና በትክክል ስራ ላይ ብትውል ኖሮ ለራሳችንም ሆነ ለዓለም ማድረግ ለምንፈልገው ነገር ሁሉ ጊዜ ይኖረን ነበር። በእያንዳንዱ የገንዘብ አወጣጥ፣ በጊዜ፣ በጉልበትና በአጋጣሚዎች አጠቃቀም እያንዳንዱ ክርስቲያን ለአመራር ወደ እግዚአብሔር ይመልከት። “ከእናንተ ማንም ጥበብ ቢጎድለው ሳይቆጥብ ለሁሉም በልግስና የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፣ ይሰጠዋልም::” Ministry of Healing, P. 206-208.MYPAmh 207.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents